Fana: At a Speed of Life!

በጋምቤላ ክልል በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች የህዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት እንዲሰሩ ተጠየቀ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 19 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በጋምቤላ ክልል ያለውን ሰላም በማጠናከር የህዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በየደረጃው የሚገኙ የአመራር አካላት በቁርጠኝነት ሊሰሩ እንደሚገባ የክልሉ ምክር ቤት ጠየቀ።

የክልሉ ምክር ቤት ስድስተኛ የስራ ዘመን 11ኛ መደበኛ ጉባኤ ዛሬ በጋምቤላ ከተማ ተጀምሯል።

አፈ-ጉባኤው አቶ ጁል ናንጋል ጉባኤውን ሲከፍቱ፤ በክልሉ ያለውን ሰላም ይበልጥ አስተማማኝ በማድረግ የህዝቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚዊ ፍላጎት ለማረጋጥ አመራሩ ጠንክሮ ሊሰራ ይገባል ብለዋል።

መጪው ሀገር አቀፍና ክልላዊ ምርጫ ፍጹም ሰላማዊና በህዝብ ዘንድ አመኔታ ያለው ሆኖ እንዲጠናቀቅ ከአመራሩ የላቀ ኃላፊነት እንደሚጠበቅም አስረድተዋል።

በክልሉ በሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምርጫው ሰላማዊ በሆነ መልኩ ፍፃሜውን እንዲያገኝም የጀመሩትን ተቀራርቦ የመስራት ተግባር  አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸውም ማሳሰባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በተጨማሪም እየጨመረ የመጣውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመከላከል የምክር ቤት አባላትና በየደረጃው የሚገኙ አስፈፃሚ አካላት ህዝቡን በማስተባበር ተግተው ሊሰሩ እንደሚገባም አሳሰበዋል።

ምክር ቤቱ የወቅቱን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘቡ አዋጆችን ከማውጣት ባለፈ የልማትና የመልካም አስተዳደር እቅዶች በአግባቡ እንዲተገበሩ አስፈፃሚ አካላትን የመከታተልና የመቆጣጠር ስራውን አጠናክሮ እንደሚያስቀጥል አረጋግጠዋል።

ጉባኤው ለሶስት ቀናት በሚኖረው ቆይታ ያለፈውን ግማሽ በጀት ዓመት የክልሉን የልማትና የመልካም አስተዳደር፣ የክልሉን ጠቅላይ ፍርድ ቤትና የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤቶች የእቅድ ክንውን ሪፖርት አዳምጦ እንሚያጸድቅ ይጠበቃል።

በተጨማሪም የቀጣይ ግማሽ በጀት ዓመት የተከለሰ የልማትና የመልካም አስተዳር እቅድ፣ የአምስት ረቂቅ አዋጆችና የተለየዩ ሹመቶችን መርምሮ እንደሚያጸድቅ ከወጣው መርሃ ግብር ለማወቅ ተችሏል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.