Fana: At a Speed of Life!

በጋምቤላ ክልል የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ሊጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በጋምቤላ ክልል የግብርናውን ልማት በማዘመን የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ሊጠናከር እንደሚገባ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ገለፁ፡፡
የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ ስር የሚገኙ ፕሮጀክቶችን የስራ ክንውን በማስመልከት ውይይትና የመስክ ምልከታ አካሂደዋል፡፡
በመስክ ምልከታው በክልሉ የሚሰሩ የአነስተኛ መስኖ ግንባታ መጓተትና የንፁህ መጠጥ ውሃ ዝርጋታ ፈጣን አለመሆን በደካማ ጎን በስፋት ተገምግመዋል፡፡
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡመድ ኡጁሉ በተለይም የአነስተኛ መስኖ ግንባታ መጓተት ምላሽ ማግኘት እንዳለበት አንስተዋል፡፡
እንደ አንድ ተግዳሮት ለሚነሳው የሲሚንቶ እጥረት የክልሉ መንግስት አቅርቦት እንዲመቻች በማድረጉ ይህን አጋጣሚ በመጠቀም ግንባታቸውን ማጠናቀቅ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
የክልሉን ህዝብ የልማት ተጠቃሚ ለማድረግ እየተደረገ ባለው ጥረት ባለድርሻ አካላት የተጀመሩ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው የጊዜ ሰሌዳ ተጠናቀው ለአገልግሎት እንዲበቁ ሃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡
የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ ኡጁሉ ሏል በወረዳዎች በተለይም በግብርናው ዘርፍ ተጀምረው ፍፃሜ ያላገኙና ግንባታቸው የተጓተቱ ስራዎች ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በርካታ ፕሮጀክቶች እንደመገኘታቸው መጠን የተፈለገውን የህብረተሰብ የመልማት ጥያቄ ለመመለስ በሚደረገው ጥረትም ባለድርሻ አካላት በጋራ እንዲሰሩ ማሳሰባቸውን ከጋምቤላ ክልል መንግስት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.