Fana: At a Speed of Life!

በጋምቤላ ክልል የአምራች ኢንዱስትሪውን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ያለመ ንቅናቄ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል የአምራች ኢንዱስትሪውን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ እና የዘርፉን ኢንቨስትመንት ለማበረታታት ያለመ የንቅናቄ መድረክ ተካሂዷል፡፡
መድረኩ “ኢትዮጵያ ታምርት” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ሲሆን÷ የአምራች ኢንዱስትሪውን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ብሎም የዘርፉን ልማት ለመደገፍ የተዘጋጀ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ በመድረኩ ላይ እንደገለጹት÷ ንቅናቄው ኢንዱስትሪዎች ለሀገር ውስጥ ምርት እድገት እያበረከቱ ያለውን አስተዋፅኦ እንደሚያሳድግ ተስፋ የተጣለበት ነው ብለዋል፡፡
በክልሉ ያለውን የውሃ ሀብት የኢንዱስትሪ ጥሬ እቃ አድርጎ በመጠቀም ለታሸገ ውሃ ማምረቻ፣ ለፈሳሽ ሳሙና ምርት እንዲሁም በአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንዱስትሪ የሚመረቱ ምርቶችን በማምረት የክልሉን ሕዝብ ተጠቃሚ ማድረግ ይቻላል ብለዋል፡፡
በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ የሚታዩ ችግሮችን በመለየትና መረጃዎችን በማደራጀት የክልሉ መንግስት ዘርፉን ለማሳደግ በትኩረት ይሰራል ማለታቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ንቅናቄው የአምራች ኢንዱስትሪውን አቅም ለመገንባትና የአገር ውስጥ ተተኪ ምርቶችን ለማሳደግ አወንታዊ ሚና እንደሚኖረውም ተመላክቷል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.