Fana: At a Speed of Life!

በጋምቤላ ክልል የፈጠራ ዝንባሌና ተነሳሽነት  ያላቸውን ወጣቶች ጥረታቸውን ማገዝ እንደሚገባ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ሰኔ 28፣2014 (ኤፍ ቢሲ) በጋምቤላ ክልል የፈጠራ ዝንባሌና ተነሳሽነት ያላቸውን ወጣቶች ጥረታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ለማስቻል ሁሉም የድርሻውን ሊያበረክት እንደሚገባ ተገለፀ።

ከክልል፣ ከወረዳ እና ከዞን ለተውጣጡ ባለድርሻ አካላት በፈጠራ ስራ ዙሪያ ግንዛቤ ለማሳደግና  ወጣቶችን ለማበረታታት በክልሉ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ አዘጋጅነት የጋራ መድረክ  ተካሂዷል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ  ስለ ሰው ልጅ ስልጣኔ እና የዕድገት ደረጃ ሲታሰብ ስለፈጠራ ማስታወስ ግድ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የሰው ልጅ ቁሳዊም ሆነ አካላዊ እድገት ከፈጠራ ጋር የተያያዘ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ በዓለም ላይ አዳዲስ እና አስደናቂ ፈጠራዎች እያታዩ መሆኑንም ነው የጠቆሙት።

ርዕሰ መስተዳድሩ አክለውም በኤሌክትሪክ ሲቲ ፣ በመካኒካል ሙያ እና በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጅ የተለያዩ አዲስ ፈጠራ  ያበረከቱ ወጣቶችን በማበረታታት ጥረታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ሁሉም የድርሻውን ሊያበረክት ይገባል ብለዋል፡፡

የፈጠራ ዝንባሌ ያላቸው ወጣቶች ሲገኙ ልዩ ትኩረት በመስጠት እና ክትትል በማድረግ የጀመሩትን ጥረት አጠናክረው እንዲቀጥሉ  የክልሉ መንግስትም አስፈላጊውን  ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

በእለቱ የተለያዩ የፈጠራ ውጤቶችን የሰሩ ወጣቶችን ለማበረታታት ከ8 ሺህ እስከ 15 ሺህ ብር ሽልማት የተበረከተላቸው መሆኑን ከጋምቤላ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.