Fana: At a Speed of Life!

በጋሞ ዞን ከ600 ሚሊየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋሞ ዞን በተለያዩ የልማት ዘርፎች ለመሰማራት ከ600 ሚሊዮን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መስጠቱን የዞኑ ኢንቬስትመንት ማስፋፊያ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
 
በጽህፈት ቤቱ የመሬት አቅም ጥናት ፕሮሞሽን ሥራ ሂደት ባለሙያ ወይዘሮ ፍቅርተ ዘሪሁን÷ ባለሃብቶቹ ፈቃዱ የተሰጠው በዞኑ በተለያዩ የልማት ዘርፎች ለመሰማራት ያቀረቧቸው 27 የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች ተቀባይነት በማግኘታቸው መሆኑን ተናግረዋል።
 
ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃዱን የወሰዱት በግብርና፣ በኢንዱስትሪና በተለያዩ የአገልግሎት መስጫ ዘርፎች ለመሰማራት ነው ብለዋል።
 
በዚህ መሰረትም በገጠር ወደ 600 ሄክታር የሚጠጋ በከተሞች ደግሞ 14ሺህ 950 ካሬ ሜትር መሬት በመስጠት መሬት መሰጠቱን ወይዘሮ ፍቅርተ ተናግረዋል።
 
ባለሙያዋ እንዳሉት አብዛኞቹ ባለሀብቶች የግንባታ ሥራ የጀመሩ ሲሆን ቀሪዎቹ ዝግጅት ላይ እንደሆኑ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
 
ባለሃብቶቹ ግንባታቸውን አጠናቀው በሙሉ አቅማቸው ምርትና አገልግሎት መስጠት ሲጀምሩም ለ12 ሺህ ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል እንደሚፈጥሩም አስታውቀዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.