Fana: At a Speed of Life!

በጋሸና እና ሌሎች ግንባሮች የተቀዳጀነው ድል አሸናፊነታችን ቅርብ መሆኑን ያሳያል – የቀድሞ ሰራዊት አባላት

አዲስ አበባ፣ ህዳር 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው እለት በጋሸናና ሌሎች ግንባሮች በወገን ጥምር ሃይል የተመዘገበው ድል የኢትዮጵያውያን አሸናፊነት ስለመቅረቡ የሚያሳይ ነው ብለዋል የቀድሞ ሰራዊት አባላት።
 
ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት እና ለ22 ዓመታት የቀድሞ ሰራዊትን ያገለገሉት ሻለቃ ወንዱ ገዛኸኝ እንዳሉት፥ የዛሬው የጋሸና እና ሌሎች አካባቢዎች ድል የኢትዮጵያ ሃይሎች አብዛኛውን ውጊያ እንዳሸነፉ የሚጠቁም ነው።
 
ሌላኛው የቀድሞ ሰራዊት አባልና በሰራዊቱ ከ9 ዓመት በላይ ያገለገሉት 10 አለቃ አብነት ምትኩ በበኩላቸው በሰጡት አስተያየት፥ የስፍራዎቹ ገዥ መሬትነት፥ ለቀጣይ ጉዞ ቀልጣፋ እና በጥቂት መስዋዕትነት እንዲሳካ በር የሚከፍት ነው ብለዋል።
 
ጦርነቱ ወደ ማለቂያው እየሄደ ማሳያ መሆኑን ያነሱት የቀድሞ ሰራዊቱ አባላት፥ የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች ጠብመንጃቸውን አስቀምጠው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሆደ ሰፊነት እና በያገባኛል ስሜት በሰላም እጅ ስጡ ያሉትን እድል ቢጠቀሙ ይጠቅማቸዋል ብለዋል።
 
እስካሁን የተገኙት ድሎች እንዲቀጥሉም ሁሉም ዜጎች በሁሉም ግንባሮች ከመከላከያና ከሌሎች የጸጥታ ሀይሎች ጎን እንዲቆሙ እና አካባቢያቸውን በንቃት እንዲጠብቁ ነው ጥሪ ያስተላለፉት።
 
የወገን ጥምር ሃይል በ“ዘመቻ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት” በወሰደው የማጥቃት እርምጃ በጋሸና ግንባር አርቢት፣ ጋሸናና ሌሎች አካባቢዎችን ነፃ ማውጣቱ ዛሬ መገለፁ ይታወቃል።
 
በዚህ ዘመቻ በአጭር ቀናት ውስጥ አስደናቂ ውጤቶች መዝገባቸውን የገለፀው መንግስ፥ ጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ሃይል፣ ሚሊሻና ፋኖ በጥምረት ባደረጉት ተጋድሎ በጋሸና ግንባር የአርቢትን፣ የአቀትን እና የጋሻና ከተሞችን በቁጥጥር ስር አውለዋል ነው ያለው።
 
የወገን ጦር ጋሸናንና አካባቢውን ከመቆጣጠር አልፎ በላሊበላ፣ ወልዲያና ወገልጤና አቅጣጫ ወደ ፊት እየገሰገሰ እንደሚገኝም ተገልጿል።
 
አፈወርቅ አለሙ
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.