Fana: At a Speed of Life!

በጌዴኦ ዞን ቡሌ የምርጫ ክልል ከ12 ሰዓት ጀምሮ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)በጌዴኦ ዞን ቡሌ የምርጫ ክልል የሚደረገው ዳግም ምርጫ ከ12 ሰዓት ጀምሮ እየተካሄደ ይገኛል።

በምርጫ ክልሉ በአጠቃላይ 83 የምርጫ ጣቢያዎች ያሉ ሲሆን÷ በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች አስፈላጊ ቁሳቁስ መሰራጨቱን የጌዲኦ ዞን ምርጫ ቦርድ አስተባባሪ አቶ ሲሳይ አበባየሁ ገልጸዋል።

ከጸጥታ ጋር በተያያዘ ሰላማዊ መሆኑን አንስተው በሁሉም ጣቢያዎች የጸጥታ አካላት መመደባቸውን አስታውቀዋል።

በምርጫ ክልሉ 3 የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚሳተፉ መሆናቸውን ገልፀው÷ ብልጽግና፣ ጌህዴድ እና ኢዜማ መሆናቸውን መናገራቸውን ደሬቴድ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.