Fana: At a Speed of Life!

በጌዴኦ ዞን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተጀመረ

 

አዲስ አበባ፣ህዳር 17፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል ጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ በወጣት አደረጃጀት አስተባባሪነት “እኔም የዘማች ቤተሰብ አካል ነኝ̍” በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት በወጣቶች እና በክልል ከፍተኛ አመራሮች በይፋ ተጀመረ::

ኢትዮጵያውያን ጀግኖችን የወለዱ፣ ለአገራቸው የሚዋጉ እና ጠላትን የሚያንበረክኩ ጀግና እናቶች አሉን ሲሉ የደቡብ ክልል ወሳኝ ኩነቶች ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ተስፋዬ አጋፋሪ ተናግረዋል፡፡

የዞኑ ወጣቶች የአገራቸውን ጥሪ ተቀብለው ከአገር መከላከያ ጎን መሰለፍ እና ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ ማድረግ ይገባቸዋል ያሉት በምክትል ማዕረግ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዮት ደምሴ ናቸው፡፡

የአካባቢን ሰላም በመጠበቅ እና የዘመቱ ወንድም እህቶችን ቤተሰብ በመንከባከብ ወጣቶች ስራዎችን እያከናወኑ እንደሚገኙም ገልጸዋል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ጦር ግንባር መዝመት ወጣቶች ላይ ትልቅ መነቃቃት ፈጥሯል ያሉት አስተዳዳሪው÷ ወጣቶች ወደ ግንባር ለመዝመት ዝግጅት ላይ እንደሚገኙም ተናግረዋል።

በዞኑ የተጀመረው የመከላከያ ሰራዊት እና የዘማች ቤተሰብ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስተዳዳሪው ገልጸዋል።
ወጣቶች የአካባቢያቸውን ሰላም በመጠበቅ፣ ሰርጎ ገቦችን በማጋለጥ የአገር አለኝታነታቸውን እያረጋገጡ እንደሚገኙ የክልሉ ወጣቶች ፌደሬሽን ተቀዳሚ ፕሬዚዳንት ዘላለም ጠቁመዋል።

ወጣቱ በተሰማራበት መስክ ውጤታማ እንዲሆን ለአገር መከላከያ ሰራዊት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል።

ዛሬ በተካሄደው መርሃ ግብር ለመከላከያ ሰራዊት የደም ልገሳ የተደረገ ሲሆን፥ የዘማች ቤተሰብ ቤት ጥገናና ድጋፍ ተከናውኗል።

በማስተዋል አሰፋ

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.