Fana: At a Speed of Life!

በጌዴኦ የቡና ምርታማነትንና ጥራትን ለማሳደግ ጥረት እየተደረገ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጌዴኦ ዞን የቡና ምርታማነትና ጥራትን ለማሳደግ የኩታ ገጠም አሰራርን በመተግበር ጭምር ጥረት እየተደረገ መሆኑን የዞኑ ግብርና ልማት መምሪያ አስታወቀ።

ከዞኑ የተውጣጡ አርሶ አደሮች፣ አመራሮችና የግብርና ባለሙያዎች በዲላ ዙሪያ ወረዳ በኩታ ገጠም የለማ የቡና እርሻ በመጎብኘት የልምድ ልውውጥ አድርገዋል።

የጌዴኦ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና ልማት መምሪያ ኃላፊ ዶክተር ዝናቡ ወልዴ በዚህ ወቅት እንዳሉት፥ አርሶ አደሩ ሁሉ አቀፍ የቡና ምርታማነት መሻሻያ ፓኬጅ እንዲጠቀም በንቅናቄ እየተሰራ ነው።

በተለይ የምርት መቀነስ ችግርን ለመከላከል ያረጀ ቡና በሚበዛባቸው ዲላ ዙሪያ፣ ወናጎና ይርጋጨፌ ወረዳዎች የቡና ጉንደላና እድሳት እንዲሁም የቡና ተከላ በኩታ ገጠም እየተስፋፋ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህም ባለፈው ዓመት የተተከሉ የተሻሻሉ ዝርያ ያላቸው ከ15 ሚሊየን በላይ ችግኞች እንክብካቤ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ አስታውቀዋል።

በመጀመሪያ ዙር ምርት ለመሰብሰብ አራትና ከዚያ በላይ ዓመታት ያስጠብቅ የነበረውን ጊዜ ሙሉ የቡና ፓኬጅ ተግባራዊ በማድረግ ከሁለት ዓመታት ባነሰ ጊዜ ምርት እንደተገኘም ጠቅሰዋል።

በጉብኝቱ በቀሰሙት ዕውቀት የተሻሻሉ የቡና ዝርያዎች ከሌሎች አርሶ አደሮች ጋር በኩታ ገጠም በማልማት ተጠቃሚ ለመሆን እንደሚጥሩ ገልጸዋል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.