Fana: At a Speed of Life!

በግማሽ ዓመቱ 442 ሚሊየን 782 ሺህ ብር የሚያወጡ ቁሳቁሶች ጉዳት ላጋጠማቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ ተደርጓል- አቶ ላቀ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኮንትሮባድ ዝውውሩ የሚያዙና የህዝብ ሀብት የሆኑ የተለያዩ ቁሳቁሶችን በሰው ሠራሽና በተፈጥሮ ችግር ጉዳት ላጋጠማቸው አካባቢዎችና የማህበረሰብ ክፍሎች ግምታዊ ዋጋቸው 442 ሚሊየን ብር 782 ሺህ 998 ብር የሚያወጡ ቁሳቁሶች ድጋፍ መደረጉን የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው አስታወቁ፡፡

በዚህም የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን ሞት ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል ችግር ለደረሰባቸው የማህበረሰብ አካላት፣ በአፋር ክልል በጎርፍ መጥለቅለቅ ለተገጎዱ ወገኞች፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ፣ በአማራ ክልል በጎርፍና በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች፣ ለኢትዮጵያ አደጋ ሥራ አመራር እና ለሀገር መከላከያ ሠራዊትና ለአማራ ልዩ ኃይል ድጋፍ መደረጉን ጠቁመዋል።

እንዲሁም ከመተከል ዞን ለተፈናቀሉ የማህበረሰብ ክፍሎች፣ በወላይታ ዞን በሶዶ ከተማ ንብረታቸው በቃጠሎ ለወደመባቸው ዜጎች እና ለተለያዩ ተቋማትና ድርጅቶች ልዩ ልዩ ቁሳቁሶችን ድጋፍ እንደተደረገም ነው የገለፁት።

በአጠቃላይ ” የህዝብን ሀብት ለህዝብ ” በሚለው መርህ መሰረት ከላይ የተጠቀሰው 442 ሚሊየን ብር 782 ሺህ 998 ብር የሚያወጡ ልዩ ልዩ ቁሳቁሶች ለህዝብ በቀጥታ መድረሱን አስረድተዋል፡፡

ይህ በጎ ሥራና ማህበራዊ ኃላፊነት በተግባር እንዲከወን የገቢዎች ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት አመራሮች፣ ሠራተኞችና አጋር አካላት ላደረጉት ትብብር ምስጋና አቅርበዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.