Fana: At a Speed of Life!

 በግሪክ ስደተኞች ተቃውሞ ላይ ናቸው

አዲስ አበባ ፣ ጥር 26 ፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) በግሪኳ ሌስቦስ ደሴት የሚገኙ ስደተኞች ተቃውሞ ላይ ናቸው።

ስደተኞች በአያያዝ ሁኔታ ላይ ባላቸው ቅሬታ ለተቃውሞ መውጣታቸው የተገለፀ ሲሆን÷  የግሪክ ፖሊስም ተቃዋሚዎችን ለመበተን  አስለቃሽ ጭስ  መተኮሱ ተነግሯል፡፡

ሴቶችን እና ሕፃናትን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ወደ ሚትለን ከተማ ለመዘዋወር ሙከራ አድርገዋል ፡፡

የስደተኞቹ ተቃውሞ የተነሳው የግሪክ መንግሥት በባህር ወደ ሀገሪቱ የሚመጡ ስደተኞችን ለመከላከል የውሃ ላይ መሰናክል እንዲሰራ የሚያደርግ አቅድ በማቅረቡ ነው ተብሏል።

ስደተኞች አውሮፓ ለመግባት ብዙውን ጊዜ በቱርክ በኩል በማድረግ ግሪክ የሚደርሱ ሲሆን ይህም ለአስተዳደር አስቸጋሪ እንደሆነ ተጠቁሟል።

በርካቶዎቹ ስደተኞች ከአፍጋኒስታን እና ሶሪያ መሆናቸውን የገለፀው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስደተኞቹ ግጭቶች እና መድሎዎችን በመሸሸ ግሪክ የሚደርሱ ናቸው

ለ700 ስደተኞች ብቻ ታስቦ በተሰራው የመጠለያ ካምፖ በአሁኑ ወቅት ውስጥ 7 ሺህ 200 የሚሆኑ ስደተኞች ይገኛሉ ተብሏል።

ምንጭ፡-ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.