Fana: At a Speed of Life!

በግብርናው ዘርፍ የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ ባለ ድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል-አቶ ዑመር ሁሴን

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በግብርናው ዘርፍ አመርቂ ውጤት ለማስመዝገብ ባለ ደርሻ አካላት በቅንጅት መስራት እንደሚገባቸው የግብርና ሚኒስትር አቶ ዑመር ሁሴን ገለጹ፡፡
 
ሚኒስትሩ “ግበርና ለኢኮኖሚ ዋስትና” በሚል መሪ ሀሳብ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ÷ 11 ነጥብ 4 ሚሊየን ሄክታር የሚሆን ምርት በተቀመጠለት ጊዜ መሰብሰቡን ተናግረዋል፡፡
 
የምርት አሰባሰብ ችግር ለግብርና ምርት ብክነትና ለምርት መቀነስ መንስኤ እንደሚሆን የገለጹት ሚኒስትሩ ÷ ይህን ችግር ለማቃለል ከ1 ሺህ 300 በላይ ኮምባይነሮችን እና የተለያዩ ተክኖሎጂዎችን በመጠቀም ሰብልን በአጭር ጊዜ መሰብሰብ ተችሏል ብለዋል።
እስካሁንም በአገር አቀፍ ደረጃ ከ300 መቶ ሚሊየን ኩንታል በላይ የእህል ምርት መሰብሰቡን ነው የተናገሩት፡፡
 
ጦርነቱ በተካሄደባቸው ክልሎች የግብርና ስራው ክፉኛ ተፈትናል ያሉት አቶ ኡመር÷ በተመሳሳይ በአርብቶ አደሮች አካባቢ የተከሰተው ድርቅ በእንስሳት ሃብት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡
 
በሌላ በኩል የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ስራ በበርካታ የሀገሪቱ አካባቢዎች ባህል እየሆነ መምጣቱን ጠቁመው÷ እንደ ሀገር 400 ሺህ ሄክታር መሬት ለማልማት እቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል፡፡
 
በአርሶ አደሩ ዘንድ የሚፈጠርን የማዳበሪያ እጥረት ችግር ለመቅረፍ የግልና የመንግስት የልማት ድርጅቶች ስራውን እንዲሰሩ ሁኔታዎችን ማመቻቸት እንደሚያስፈልግም ነው በአጽንኦት የገለጹት፡፡
 
ሀገር ውስጥ መመረት የሚችሉ ከውጪ የምናስገባቸው ምርቶች የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ ገቢ አሟጠው ሲወስዱ ይስተዋላል ያሉት ሚኒስትሩ÷ ችግሩን ለማስወገድ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
 
ግብርናው አመርቂ ውጤት እንዲያስመዘግብም የዘርፉ ተዋናዮች እና ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት እንዳለባቸው ነው አቶ ዑመር ያሳሰቡት፡፡
 
በሻምበል ምህረት
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.