Fana: At a Speed of Life!

በግዕዝ ቋንቋ ሥርዓተ ትምህርት ቀረፃ ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የግዕዝ ቋንቋ ትምህርትን ወጥ በሆነ መልኩ መስጠት የሚያስችል የሥርዓተ ትምህርት ቀረፃ ውይይት በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው።

ውይይቱ የግዕዝ ቋንቋን ከተጋረጠበት አደጋ ለመታደግ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚያደርጉትን ጥረት ወጥ በሆነ መልኩ ለማስቀጠል ያለመ ነው ተብሏል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ በየከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ ወጥ የሆነ የግዕዝ ቋንቋ የትምህርት አሰጣጥ እንዲኖር ለማድረግም በመሠረታዊው የቋንቋው ይዘት ዙሪያ ውይይት እየተደረገበት ይገኛል።

ውይይቱ ለሶስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን፥ ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር፣ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴርና ከተለያዩ ጥናትና ምርምር ተቋማት የተውጣጡ ምሁራን እየተሳተፉ መሆኑን የአማራ መገናኛ ብዙሃን ድርጅት ዘገባ ያመላክታል።

የቋንቋ ትምህርቱ ከዚህ ቀደም በተወሰኑ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መሰጠት ቢጀምርም፥ ተቋማቱ የራሳቸውን መለስተኛ ጥናት ብቻ መሠረት አድርገው መሥራታቸው ክፍተት መፍጠሩ በውይይቱ ወቅት ተገልጿል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.