Fana: At a Speed of Life!

በግድቡ ላይ በሚደረገው ድርድር ዋሽንግተን ሀገራቱ በራሳቸው መፍትሄ እንዲያስቀምጡ ብቻ ትደግፋለች- ማይክ ፖምፔዮ

አዲስ አበባ፣የካቲት10፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)  በህዳሴው ግድብ ላይ እየተደረገ ባለው ድርድር ዩናይትድ ስቴትስ ሀገራቱ በራሳቸው መፍትሄ እንዲያስቀምጡ ብቻ ድጋፍ እንደምታደርግ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፔዮ ገለፁ።

የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው እና ማይክ ፖምፔዮ በጋራ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

በዚሁ ወቅትም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ገዱ የህዳሴ ግድብን በተመለከተ የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም ባስከበረ መልኩ ሶስቱ ሀገራት ማለትም ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ ስምምነት ላይ ይደርሳሉ የሚል እምነት እንዳላቸው ነው የተናገሩት።

ዩናይትድ ስቴትስ እና የዓለም ባንክ ሀገራቱ ወደ ስምምነት እንዲመጡ እየተጫወቱ ላሉት አወንታዊ ሚናም ምስጋና አቅርበዋል።

የአሜሪካ  የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፔዮ በበኩላቸው ኢትዮጵያ የአሜሪካ ጠንካራ አጋር ሀገር መሆኗን አንስተዋል።

ይህን የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት የበለጠ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሜሪካ እንደምትሰራም ነው ያመለከቱት።

በመግለጫው ዋሽንግተን በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን የሪፎርም ስራ እንደምትደግፍም አረጋግጠዋል።

በተጨማሪም አሁን ላይ በምስራቅ አፍሪካ የተከሰተውን የአንበጣ መንጋ ለመከላከል ዩናይትድ ስቴትስ የ8 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ እንደምታደረግ ይፋ አድርገዋል።

 

በሶዶ ለማ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.