Fana: At a Speed of Life!

በግድቡ የውሃ አሞላልና አለቃቀቅ ላይ ረቂቅ የስምምነት ሰነድ ለማዘጀት ሲካሄድ የነበረው ውይይት በዚህኛውም ዙር አልተቋጨም

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከፈረንጆቹ የካቲት 12 እስከ 13 ቀን 2020 በዋሽንግተን ዲ.ሲ. የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የውሃ አሞላል እና አለቃቀቅን በተመለከተ ረቂቅ የስምምነት ሰነድ ለማዘጀት ሲካሄድ የነበረው ውይይት ሳይቋጭ ማምሻውን ተጠናቀቀ።

በውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ የተመራው የኢትዮጵያ ልኡክ በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ከግብፅ እና ሱዳን ልዑካን ጋር የተደረገውን የህግ ማዕቀፍ ድርድር ውጤት በዋሽንግተን ዲሲ ከገመገመ በኋላ ሌላ ዙር በኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ መካከል ውይይቱ ቀጥሎ ነበር።

በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍፁም አረጋ ማምሻውን እንዳስታወቁት፥ ሀገራቱ  የግድቡን የውሃ አሞላል እና አለቃቀቅን በተመለከተ ረቂቅ የስምምነት ሰነድ ለማዘጀት ሲያደርጉት የነበረው ውይይት በዚህኛውም ዙር አልተቋጨም።

አምባሳደሩ ቀጣይ ሂደቱ ምን እንደሚሆን በፌስቡክ መልዕክታቸው ላይ አላካተቱም።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.