Fana: At a Speed of Life!

በጎባ ከተማ የጦር መሳሪያ በመደበቅና በማዘዋወር የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 17 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጎባ ከተማ የጦር መሳሪያ በመደበቅና በማዘዋወር የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖሊስ አስታወቀ።
የከተማዋ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ምክትል ዳይሬክተር ዋና ሳጅን እንግዳ አምሃ እንደገለጹት፥ ፖሊስ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መመሪያ መሰረት ባካሄደው በቤት ለቤት ፍተሻ የጦር መሳሪያ ደብቀው የተገኙ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር አውሏል።
በተመሳሳይ በከተማ የእንቅስቃሴ ፍተሻ ዘመቻ የጦር መሳሪያ ሲያዘዋውሩ የተገኙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል።
ከተያዙት መሳሪያዎች ውስጥ ክላሽንኮቭ ጨምሮ የተለያዩ ጠብመንጃዎች፣ ሽጉጦች፣ የጦር ሜዳ መነጽርና ተተኳሽ ጥይቶች እንደሚገኙ መጥቀሳቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.