Fana: At a Speed of Life!

በጎንደር ከተማ ለዘማች ቤተሰቦች ከ1 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የከተማ አስተዳደርሩ ወራሪውንና አሸባሪውን ህወሓት ለመፋለም ወደ ግንባር የዘመቱ ጀግኖችን ቤተሰቦች በተለያየ መንገድ እየደገፈ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ የዘማቾች መልሶ ማቋቋም ዐቢይ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አዝመራው ተዘራ ገልጸዋል።
በተለያዩ ግንባሮች ዘምተው የተሰው ጀግኖችን ልጆችና ቤተሰቦች ነፃ የትምህርት ዕድል በተለያዩ የትምህርት ተቋማት እንዲያገኙ ከማድረግ በተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ መደረጉንም ነው የገለጹት።
በዚህም ከከተማዋ ባለሀብቶች በተሰበሰበ ገንዘብ÷ ለተሰው የአገር ባለውለታ ቤተሰቦች ከአንድ ሚሊየን ብር በላይ ገንዘብ ድጋፍ መደረጉን አቶ አዝመራው ገልጸዋል፡፡
የክልሉን መንግስት ጥሪ ተቀብለው ወደ ግንባር ለዘመቱ ቤተሰቦች ሀብት በማሰባሰብ ድጋፍ የማድረጉ ተግባር መቀጠሉን የተናገሩት ሰብሳቢው÷ በዘላቂነት ለማቋቋም የልየታ ስራ እየተከናወነ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
በዞብል ክፍለ ከተማ ለሀምሳ ዘማች ቤተሰቦች ልዩ ልዩ ድጋፍ መደረጉን የተናገሩት ደግሞ የክፍለከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ገብረሚካኤል አየልኝ ናቸው።
በክፍለከተማው ለ30 ዘማች ቤተሰቦች 60 ሺህ ብር ድጋፍ ተደርጓል ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚው÷ ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
ድጋፍ የተደረገላቸው የዘማች ቤተሰቦችም÷ የእኛ ቤተሰቦች ወደ ግንባር ጠላትን ለመፋለም ቢዘምቱም መንግሥትና ህዝቡ የሚያደርግልን ድጋፍ ተጨማሪ ብርታት ሰጥቶናል ነው ያሉት።
ለዘማች ቤተሰቦች የከተማው ማህበረሰብ የሚያደርገውን ድጋፍ በተሻለ ደረጃ እንዲቀጥልም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በምናለ አየነው
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.