Fana: At a Speed of Life!

በጎንደር ከተማ በህገ ወጥ ድርጊት በተሳተፉ የፀጥታ አካላት ላይ እርምጃ የመወስዱ ተግባር ይቀጥላል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጎንደር ከተማ በህገ ወጥ ድርጊት በተሳተፉ የፀጥታ አካላት ላይ እርምጃ የመወስዱ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ዘውዱ ማለደ ተናገሩ፡፡

በከተማዋ የሚፈፀመውን ህገወጥ ድርጊት የመከላከል እና የፀጥታ ሁኔታውን ወደ መደበኛ ሁኔታ የመመለስ ተግባር አዲስ የተዋቀረው ካቢኔ ቀዳሚ ተግባር መሆኑን ነው ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው በተለይ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፓሬት ተናገሩት፡፡

በህገወጥ ጥይት ተኩስና በሰው ማገት ወንጀል በሚሳተፉ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን ያነሱት ምክትል ከንቲባው በተለያየ አደረጃጀት በመሳተፍ ህገወጥ ድርጊት በሚፈፅሙ የፀጥታ አካላት እርምጃ መውሰድ ተጀምሯል ብለዋል።

አያይዘውም የከተማዋ የፀጥታ ሁኔታ በዘላቂነት እስኪፈታ ድረስ ሁለት ቦታ በሚረግጡ የፀጥታ መዋቅር አባላት ላይ በማጣራትና መረጃ በማደራጀት የተጠናከረ እርምጃ የመወስዱ ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

የከተማዋን የፀጥታ መደፍረስ እንደምቹ አጋጣሚ በመጠቀም በከተማዋ በተለያዩ አካባቢዎች የሚፈፀመውን ህገወጥ የመሬት ወረራ ድርጊትም መንግስት በመከታተል የማስቆም ስራ እየሰራ እንደሆነ አቶ ዘውዱ ገልፀዋል።

የከተማዋን ፀጥታ ወደ መደበኛ ሁኔታ ለመመለስ በሚደረግው ጥረት ህዝቡ መተባበር አለበት ያሉት ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው በማንኛውም ህገወጥ ድርጊት የሚሳተፍ አካላትን ለፀጥታ ሀይሉ መጠቆም አለበት ብለዋል፡፡

በምናለ አየነው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.