Fana: At a Speed of Life!

በጎንደር ከተማ የጥምቀት በዓልን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ ባዛር ተከፈተ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጎንደር ከተማ የጥምቀት በዓልን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀው የንግድና ትርዕት ባዛር ተከፈተ።
የጎንደር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ዘውዱ ማለደ በመክፈቻ ዝግጁቱ ላይ፥ ባዘሩ መካሄዱ በኮሮና ቫይረስ እና በጦርነቱ የተጎዳውን የከተማዋን የንግድ እንቅስቃሴ ለማነቃቃት ያግዛል ብለዋል።
የከተማዋ ነዋሪዎች እና የጥምቀትን በዓል ለመታደም በጎንደር ከተማ የሚገኙ እንግዶች በባዛሩ እንዲሳተፉ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው ጠይቀዋል።
በተለየ መንገድ በጥምቀት የምትሞሸረው የጎንደር ከተማ የተለያዩ ሁነቶችን በበዓሉ ሳምንት የምታስተናግድ ሲሆን፥ ይህ ባዛርም የፕሮግራሙ አንድ አካል መሆኑ ተገልጿል።
በንግድ ትርኢት እና ባዛሩ 80 የውጭ እና ከ200 በላይ የሀገር ውስጥ ነጋዴዎች የሚሳተፉ ሲሆን፥ ከሚገኘው ገቢ 25 በመቶው ለህልውና ዘመቻው እና ለተፈናቃይ ወገኖች ይውላል ተብሏል።
በምናለ አየነው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
+2
0
People reached
0
Engagements
Boost post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.