Fana: At a Speed of Life!

በጎንደር ከተማ 5 ሺህ 241 ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የልማታዊ ሴፍቲ ኔት ፕሮግራም ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 14 ፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጎንደር ከተማ አስተዳደር 5 ሺህ 241 የህብረተሰብ ክፍሎችን በከተሞች ልማታዊ ሴፍቲ ኔት ፕሮግራም ተጠቃሚ የሚያደርግ ፕሮግራም በይፋ ተጀምሯል፡፡

የጎንደር ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ባዩ አቡሃይ እንደገለፁት÷ በውጭ ሃይሎች እየታገዘ የሚንቀሳቀሰው የህወሓት ሽብር ቡድን ወሪራ በፈፀመባቸው አካባቢዎች በሰው ልጆች ህይወት ህልፈትና በንብረት ላይ ውድመትን አስከትሏል፡፡

የወደመውን ሃብት መልሶ ለመገንባትም ሁላችንም ርብርብ ማድረግ ይኖርብናል ያሉት ምክትል ከንቲባው÷ በከተማዋ በሁለተኛው ዙር የከተሞች ሴፍቲኔት ፕሮግራም 5 ሺህ 241 የከተማዋ ነዋሪዎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተናግረዋል፡፡

የአማራ ክልል የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት አስተባባሪ አቶ ሀሰን ውህያ በበኩላቸው÷ የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም የሚገኘው ገንዘብ ከድህነት ለመውጣት በር ይከፍታል እንጅ ራሱ ከድህነት አያወጣም ብለዋል፡፡

የሴፍቲኔት ፕሮግራም የሰዎችን የስራ ዕድል ያሳድጋል ያሉት አቶ ሃሰን÷ ፕሮግራሙ የከተማዋን ልማት ለማፋጠንና የነዋሪዎችን ህይወት ለመቀየርም ፋይደው ከፍ ያለ መሆኑን ገልፀዋል።

በፕሮግራሙ የአካባቢን የፅዳትና የአረንጓዴ ልማት ስራዎችን ፣የመሰረተ ልማትና የተፋሰስ ስራዎችን ለማከናወን እንደሚያግዝ መጠቆማቸውን ከከተማው ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.