Fana: At a Speed of Life!

በጎዴና በአሶሳ ከተሞች የተሰየሙ ሁለት የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተመረቁ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጎዴ እና በአሶሳ ከተሞች የተሰየሙ ሁለት የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተመርቀው ስራ ጀመሩ።

ትምህርት ቤቶች ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ከሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ  እና ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ርዕሰ መስተዳድር አሸድሊ ሀሰን  መርቀው ስራ አስጀምረዋል።

ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ  አዲስ አበበ የሁሉም ከተማ መሆንዋን ለማረጋገጥ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችን የሚወክሉ ተግባራት ማከናወን ይገባል  ያሉ ሲሆን ዛሬ የተመረቁት የጎዴና አሶሳ ትምህርት ቤቶች ለዚህ ማሳያ ናቸው ብለዋል ።

ህብረብሄራዊ አንድነትን በማጠናከር በጋራ ለኢትዮጵያ እድገት መትጋት ያሉት  ምክትል ከንቲባዋ ለዚህ ደግሞ መጪው ትውልድ የሀገሩን ታሪክ በአግባቡ መረዳት እና ማወቅ ይኖርበታል ማለታቸውን ከከተማዋ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ተማሪዎች የተለያዩ አካባባቢዎችን ታሪክ እያወቁ እንዲያድጉ በተለያዮ የኢትዮጵያ አካባቢ ስሞች መሰየም ተገቢ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል።

የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ በበኩላቸው ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ የተመረቁት የጎዴ እና አሶሳ ትምህርት ቤቶች የኢትዮጵያውያን ህብረብሄራዊነትና አዲስ አበባ የሁሉም ከተማ መሆንዋ ማሳያ ፤ እውነተኛ ፌደራለዝም የመመስረት ፣ አብሮ የመኖር ተግባራት ናቸውም ብለዋል።

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ርዕሰ መስተዳድር  አሸድሊ ሀሰን ፤ ትምህርት ቤቶቹ ትክክለኛ ፌደራሊዝም ውሥጥ መገባቱን ማረጋገጫ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በተያያዘም በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ የተገነቡ የበሻሌ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ በህዝብ እና በመንግሥት የተሰሩ የተለያዩ የልማት ስራዎች ተመርቀዋል ።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.