Fana: At a Speed of Life!

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የተቋቋመው ግብረ ኃይል የመተከል ዞንን የፀጥታ ማስከበር ስራ ተረከበ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 19፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተቋቋመው ግብረ ኃይል የመተከል ዞንን የፀጥታ ማስከበር ስራ መረከቡን ሌፍተናል ጀኔራል አስራት ዴኔሮ አስታወቁ።

በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተቋቋመውና ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና የመከላከያ ሠራዊት አመራሮች የተካተቱበት ግብረ ኃይል በዞኑ የሕግ የበላይነትን የማረጋገጥ ስራውን ሙሉ በሙሉ ጀምሯል።

የፀጥታ ኃይሉን የሚመሩት ሌፍተናል ጀኔራል አስራት ዴኔሮ እንደገለጹት የንፁሃንን ሕይወት በማጥፋት ወንጀል የተሳተፉ ተጠርጣሪዎችን የማደን ስራው ቀጥሏል።

“በወንጀሉ የተሳተፉ ተጠርጣሪዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ በሕግ ተጠያቂ ይሆናሉ” ሲሉም ተናግረዋል።

ችግሩን ከመሰረቱ ለመፍታት በአሁኑ ወቅት በየደረጃው ከሚገኙ የማኅበረሰብ አባላትና አመራሮች ጋር ውይይት እየተካሄደ ሲሆን ወንጀለኞቹን በመለየት ለሕግ የማቅረቡ ስራም እንደሚቀጥል መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ከዚህ ጎን ለጎን የተፈናቀሉትን መልሶ የማቋቋምና የሕዝቡን የዕለት ተዕለት ኑሮ ቀድሞ ወደነበረበት የመመለስ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

ሌፍተናል ጀኔራል አስራት ዴኔሮ “በመተከል ዞን የተጀመረው የሕግ የበላይነትን የማረጋገጥ ተልዕኮ በአጭር ጊዜ ይጠናቀቃል” ብለዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.