Fana: At a Speed of Life!

በጠ/ሚ ዐቢይ መሪነት የተገኘው ድል የጠላቶቻችንን ህልም ያመከነና ቅስም የሰበረ ነው – የኦሮሚያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መሪነት በጥምር ኃይሉ የተገኘው ድል የጠላትን ህልም ያመከነና ቅስም የሰበረ መሆኑን የኦሮሚያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አስታወቀ።
ምክር ቤቱ ባወጣው መግለጫ ዘመቻ ለሕብረ ብሄራዊ አንድነት ከውጭና ከውስጥ በመቀናጀትና በመናበብ ”ኢትዮጵያን ለማፍረስ እስከ ሲኦል ድረስ እንወርዳለን”በሚል የሞኝ ፈሊጥና ትዕቢት ተወጥረው እንቅልፍ አጥተው ሲባዝኑ የከረሙ ጠላቶቻችንን ግልጽና ስውር ደባ አምክኖ የሽብርተኛዎቹን የሕወሓትና የሸኔ ቡድኖችን የተላላኪነትና የባንዳነት ህልም ያከሸፈ መሆኑን ገልጿል።
ከዚህ ባለፈም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተመራው የጥምር ጦር ኃይሉ በአንድነትና በጣምራ በወሰደው የመልሶ ማጥቃት እርምጃ በጣት በሚቆጠሩ ቀናት አኩሪና አንፀባራቂ ድል ማስመዝገቡንም ነው የገለጸው።
በዚህ የጥምር ኃይላችን አንጸባራቂ ድል በወረራ የተያዙ የአማራ እና የአፋር ክልሎች አካባቢዎች ነፃ ወጥተዋል ብሏል።
ምክር ቤቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዘመቻውን በጦር ሜዳ በአካል ተገኝተው በመምራት ላሳዩት በሳል አመራር እና ላስገኙት ድል አድናቆቱን ገልጿል።
በእርሳቸው አመራርነት በተገኘው ዘመን አይሽሬ ድልም በዴሞክራሲና በኢኮኖሚ የበለፀገች ማህበራዊ ፍትህ የሰፈነባት ታፍራና ተከብራ የምትኖር አገር ለቀጣይ ትውልድ እንደሚያስተላልፉ ጥርጥር የለንም ብሏል ምክር ቤቱ፡፡
በተጨማሪም ጥምር ሃይሉ አገርና ህዝብን ከሽብርተኞቹ በመታደግ የጠላትን ህልም በማምከን የአገራችን መጻኢ እድል በልጆቿ ሃያል ክንድ እንደሚከበር ማሳየት በመቻሉ ምስጋናውን አቅርቧል።
በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም የኤርትራ ተወላጆችና የተለያዩ የአፍሪካ አገራት ለኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን ላሳዩት አጋርነትም ምክር ቤቱ ምስጋናውን አቅርቧል።
ከዚህ ባለፈም መላው የኢትዮጵያ ህዝብ በዘር፣ በኃይማኖትና በቋንቋ ሳይከፋፈል፥ በጋራና በአንድነት በመቆም የአብራኩ ክፋይ ልጆቹን መርቆ ወደ ጦር ሜዳ በመሸኘት፣ በመዝመት፣ የዘማች ቤተሰቦችን በመንከባከብ ላደረገው አስተዋጽኦ እና ሁሉን አቀፍ ትብብርና ድጋፍም አመስግኗል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.