Fana: At a Speed of Life!

በጣሊያን ቱሪን  የኢትዮጵያ የክብር ቆንስል ተከፈተ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጣሊያን የኢትዮጵያ  አምባሳደር  ደሚቱ ሐምቢሳ በጣሊያን ቱሪን የኢትዮጵያ የክብር ቆንስልን መርቀው ከፍተዋል።

ኢንጂነር ፍራንኮ ሩቢኒ በቱሪን አዲሱ የኢትዮጵያ የክብር ቆንስል ሲሆኑ በቱሪን ፖሊቴክኒክ ዩኒቨርስቲ ኢንጂነሪንግ ሲያስተምሩ  የነበሩ እና አሁን ኤሲቲኤ የሚባል የኢንጂነሪንግ አማካሪ ድርጅትን በዳይሬክትርነት የሚመሩ መሆናቸው ተመላክቷል።

የተለያዩ አገራት የክብር ቆንስሎች፣ ምሁራን፣ የስራ ፈጣሪዎች፣ የተቋማት ኃላፊዎች እና የቢዝነስ ሰዎች የመክፈቻ ፕሮግራሙን የተሳተፉ ሲሆን ÷ አምባሳደር ደሚቱ  ለክብር ቆንስሉ እና ለተሳታፊዎች ስለ ኢትዮጵያ በተለይም በኢትዮጵያ ስላለው ሰፊ የኢንቨስትመንት እድል፣ ስለ አገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያና አስር ዓመት የኢኮኖሚ እቅድ እንዲሁም ለኢንቨስተሮች ስለሚደረገው ማበረታቻ ገለፃ አድርገዋል።

በተጨማሪም ፔድሞንቴ ብዙ ኢንዱስትሪዎች እና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ያሉባት በመሆኑ በቅርቡ ለአገራችን ጥሩ የኢንቨስትመንት አመንጪ እንደምትሆን እምነታቸውን ገልፀዋል።

የክብር ቆንስል ኢንጂነር ፍራንኮ ሩቢኒ በበኩላቸው÷ በኢትዮጵያ እና ጣሊያን ፔድሞንቴ መካከል ያለውን የንግድ፣ የኢኮኖሚ፣ የቱሪዝም እና ባህል ግንኙነት ለማጠናከር እንደሚሰሩ እና በቱሪን እና አካባቢው ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አስፈላጊውን እገዛ እንደሚያደርጉ እንዲሁም የተጣለባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ እንደሚወጡ ቃል መግባታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.