Fana: At a Speed of Life!

በጤናው ዘርፍ ወጣቶች አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ሊፈጥሩ እደሚገባ ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሁለተኛው የአፍላ ወጣቶች እና የወጣቶች ጤና ሳምንት ፎረም “ፈጠራ ለተሻለ ወጣቶችና የአፍላ ወጣቶች ጤና አገልግሎት ተደራሽነት” በሚል መሪ ቃል ተከበረ፡፡
የወጣቶች የጤና አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግና የፈጠራ ስራዎችን በማበረታታት እየተሰራ መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ ገልጸዋል፡፡
በኢትዮጵያ ከፍተኛ ቁጥር የሚይዙትን ወጣቶች በጤናው ዘርፍ የላቀ ተጠቃሚ ለማድረግ ከጎናቸው መቆም እንደሚገባም የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ህይወት ሃይሉ ተናግረዋል፡፡
በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ፕሮግራም ዳይሬክተር ጀነራል ዶክተር አብዮት ባዩ በበኩላቸው÷ የሃገራችንን ነባራዊ ሁኔታ፣ የሕዝባችንን መሰረታዊ የጤና ችግሮች፣ የጤና መሰረተ ልማቶችን ማዕከል ያደረጉ የኢኖቬሽን ስራዎች ላይ ትኩረት መስጠት ይኖርብናል ብለዋል፡፡
በጤናው ዘርፍ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመፍጠር ረገድ ወጣቶች ትልቅ ሚና መጫወት ይኖርባቸዋል ያሉት ዳይሬክተር ጀነራሉ÷ ዘርፉ የሁሉም ተቋማት ጉዳይ በመሆኑ በትብብር መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡
ሳምንቱም በተለያዩ የወጣቶችን ጉዳዮች ባካተቱ ዝግጅቶች የሚታሰብ ሲሆን÷ የመጪው ትውልድ ጤናን ለማሻሻል የዲጂታል ጤና ስርዓትን መዘርጋት ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚከበር ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.