Fana: At a Speed of Life!

በጤናው ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት እና የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ ሁሉም አካላት በኃላፊነት መስራት አለባቸው -ዶክተር ሊያ ታደሰ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጤናው ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት እና በ2015 የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ ሁሉም አካላት በኃላፊነት መስራት እንዳለባቸው የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አመላከቱ።

በጤና ሚኒስቴር የ2015 በጀት ዓመት እቅድ ውይይት ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ዶክተር ሊያ ታደሰ÷የቀጣይ በጀት ዓመት ሁሉም እቅዶች ሪፎርሙን ተከትሎ መታቀዳቸውን ተናግረዋል።

የመንግስት ክትትልና ድጋፍ በጤናው ዘርፍ መጨመሩ የተጠቆመ ሲሆን÷ በአዲሱ በጀት ዓመት መንግሥት ለጤናው ዘርፍ የበጀተው በጀት ከአምናው ጋር ሲነፃፀር ጨምሯል ነው የተባለው፡፡

ለጋሽ ድርጅቶች የሚያደርጉት ድጋፍ መቀነሱን ያስታወሱት ዶክተር ሊያ÷ የ2015 በጀት ዓመት በጀትን ችግር ፈቺ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ማዋል እንደሚገባ ጠቁመዋል።

በአርባምንጭ ከተማ የ2015 የበጀት ዓመት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እቅድ ላይ ውይይት እየተካሄደ መሆኑን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.