Fana: At a Speed of Life!

በጥቁር አንበሳ የህክምና ተማሪ የነበረችውን ሀይማኖት በዳዳን የገደላት ግለሰብ በ21 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 28፣ 2014 ( ኤፍ ቢ ሲ) በጥቁር አንበሳ የህክምና ተማሪ የነበረችውን ሀይማኖት በዳዳን ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ የገደላት ግለሰብ በ21 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን የፍትህ ሚኒስቴር ገለጸ ።
የዐቃቤ ህግ የክስ መዝገብ እንደሚያስረዳው ደግነት ወርቁ የተባለው ተከሳሽ፥ የወንጀል ህግ አንቀፅ 671 (2) ስር የተደነገገውን ድንጋጌ በመተላለፍ ግንቦት 17 ቀን 2012 ዓ .ም በልደታ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝ ሆስፒታል ግቢ ውስጥ ከሚገኝ የፋርማሲ ት/ቤት ህንፃ አራተኛ ፎቅ ቤተ-ሙከራ ውስጥ የ2ኛ ዲግሪ መመረቂያ የምርምር ስራዋን በመስራት ላይ የነበረችው ሟች ሃይማኖት በዳዳን የቤተ-ሙከራ በሩን ከፍቶ ከገባ በኋላ በሩን ከውስጥ በመቆለፍ በአሰቃቂ ሁኔታ ጉዳት በማድረስ ህይወቷ እንዲያልፍ ማድረጉ ተገልጿል።
የዋጋ ግምታቸው ከ27 ሺህ ብር በላይ የሚያወጡ ንብረቶችን መውሰዱን እና በፈፀመው ከባድ የውንብድና ወንጀል በዐቃቤ ህግ ክስ መመስረቱን ሚኒስቴሩ አስታውሷል፡፡
የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የከባድ የሰው ግድያና የውንብድና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ለተከሳሹ ክሱ ተነቦለት ድርጊቱን ስለመፈጸሙ ተጠይቆ ፥ ወንጀሉን አልፈጸምኩም ሲል የዕምነት ክህደት ቃሉን በመስጠቱ ዐቃቤ ህግ የተከሳሽን ድርጊት በበቂ ያስረዳሉ ያላቸውን ዝርዝር የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎች በማቅረቡ ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ እንዲከላከል ብይን መስጠቱም ተመላክቷል።
ይሁንና ተከሳሽ የቀረበበትን ማስረጃ ማስተባበል ባለመቻሉ ጥቅምት 11 ቀን 2014 ዓ.ም የጥፋተኝነት ውሳኔ እንደተላለፈበት ተገልጿል።
ችሎቱ በተከሳሽ ላይ የቅጣት ውሳኔ ለመስጠት ለዛሬ ታህሳስ 28 ቀን 2014 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ በመስጠቱ ምክንያት በዛሬው ዕለት የቅጣት ውሳኔ አስተላልፏል።
በዚህም መሰረት ፍርድ ቤቱ ተከሳሽ ካቀረባቸው ብዛት ካላቸው የቅጣት ማቅለያዎች ማካከል ከዚህ በፊት የጥፋት ሪከርድ የሌለበት መሆኑን እንደ አንድ የቅጣት ማቅለያ በመያዝ በእስራት እርከን 36 ስር በማሳረፍ በ21 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን ከፍትህ ሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
May be an image of 2 people, people standing and text
0
People reached
0
Engagements
Distribution score
Boost post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.