Fana: At a Speed of Life!

በጥቅምት ወር ከ53 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጥቅምት ወር ብቻ ከ53 ቢሊየን በላይ ብር መሰብሰብ መቻሉን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ሚኒስቴሩ÷ በጥቅምት ወር 56 ቢሊየን 588 ሚሊየን 899 ሺህ 862 ብር ከ73 ሣንቲም ለመሰብሰብ አቅዶ ነው 53 ቢሊየን 906 ሚሊየን 833 ሺህ 456 ብር ከ85 ሣንቲም የሰበሰበው፡፡ አፈፃፀሙም 95 ነጥብ 26 በመቶ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
ከ2013 በጀት አመት ተመሳሳይ ወር ጋር ሲነፃፀር÷ በ 9 ቢሊየን 657 ሚሊየን 313 ሺህ 974 ብር ከ 68 ሣንቲም ብልጫ የታየ ሲሆን÷ 21 ነጥብ 82 በመቶ ዕድገት ሳይቷል መባሉን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የተሰበሰበው ገቢም÷ ከሀገር ውስጥ ታክስ 42 ቢሊየን 67 ሚሊየን 793 ሺህ 289 ብር ከ29 ሣንቲም እና ከውጭ ንግድ ቀረጥና ታክስ 11 ቢሊየን 839 ሚሊየን 40 ሺህ 167 ብር ከ 56 ሣንቲም ነው፡፡
ይህ ገቢ የተሰበሰበው በሀገራዊ ወቅታዊ ችግር ምክንያት 4 ቅርንጫፎች ምንም ሳይሰሩ እና በሌሎችም ቢሆን በተገደበ እንቅስቃሴ ውስጥ በሆኑበት ሁኔታ ነው፡፡
ለእዚህ ገቢ መሰብሰብም ዜጎች በዚህ ወቅት ሰበቦችን ሳያቀርቡ ለአገራቸውና ለህዝባቸው በማሰብ በወቅቱና በትክክለኛው ጊዜ ግብራቸውን አሳውቀው በመክፈላቸው እንዲሁም በገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን አመራሮችና ሰራተኞች ከምንጊዜውም በላይ የዕረፍት ጊዜአቸውን ጨምረው በቁርጠኝነትእና በትጋት ከልብ መስራት በመቻላቸው መሆኑ ተብራርቷል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.