Fana: At a Speed of Life!

በጦርነቱ ምክንያት ከ1 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ ሆነዋል

 

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 20 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ የጥፋት ኃይሉ ህወሓት በፈጸመው ወረራ ከ1 ነጥብ 2 ሚሊየን የሚበልጡ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸውን ገለጹ፡፡

ከወር በፊት በነበረው መረጃ ከአንደኛ እስከ 12ኛ ክፍል የሚያስተምሩ ከ1 ሺህ 600 በላይ የሚሆኑ ትምህርት ቤቶች ላይ ጉዳት መድረሱንና 300 ያህሉ ሙሉ በሙሉ መውደማቸውንም ነው ሚኒስትር ዲኤታው የገለጹት።

የጥፋት ቡድኑ በከፈተው ጦርነት በትግራይ ክልል የሚገኙ አራት ዩኒቨርሲቲዎችን ጨምሮ የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ስራ ማቆማቸው ይታወቃል፡፡

በእነዚህ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ያሉ ተማሪዎችንና መምህራንን ወደሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች የመመደብ ስራ እንደተሰራም ገልፃዋል፡፡

የጥፋት ቡድኑ የከፈተውን ጦርነት በአጭር ጊዜ በመቀልበስ በቀጣይ የትምህርት ስርዓት ላይ በማተኮር መስራት ያስፈልጋል ማለታቸውን የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

የትምህርት ሚኒስቴርም በጦርነቱ የወደሙ ትምህርት ቤቶችን ወደ ቀድሞ ይዞታቸው ለመመለስ እንሚሰራ ተናግረዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.