Fana: At a Speed of Life!

በጦርነቱ ሳቢያ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የስነ ልቦና እና የአዕምሮ ጤና ድጋፍ እየተሰጠ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጦርነቱ ሳቢያ ከቀያቸው ለተፈናቀሉ እና ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የስነ ልቦና፣ የአዕምሮ ጤና እና ማህበራዊ ድጋፍ እየተሰጠ መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለጹ፡፡
 
ዶክተር ሊያ የጤና ሚኒስቴር እና የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር የተለያዩ የዘርፉ የሙያ ማህበራትን በማሳተፍ ለተጎጂዎች ድጋፍ እያደረጉ መሆኑን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡
 
ድጋፉ በተቀናጀ መልኩ እንዲሰጥና ተደራሽነቱን በማስፋት በአጭር ጊዜ ተጎጂዎችን ለመድረስ እንዲያስችል ከሚመለከታቸው የሙያ ማህበራት፣ ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት ጋር ፍሬያማ ውይይት መደረጉንም ጠቁመዋል፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለ!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.