Fana: At a Speed of Life!

በጦርነቱ የተጎዳው ኢኮኖሚ እንዲነቃቃ የግል ባለሀብቱ ተሳትፎ ሊጎለብት ይገባል-ፕሮፌሰር ሙላቱ ፍቃዱ

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጦርነቱ የተጎዳው ኢኮኖሚ እንዲነቃቃ የግል ባለሀብቱ ተሳትፎ ሊጎለብት እንደሚገባ በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ሱዋኔ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ መምህር የሆኑት ፕሮፌሰር ሙላቱ ፍቃዱ ተናገሩ።
 
ፕሮፌሰር ሙላቱ መንግሥት በጦርነት የተቀዛቀዘውን ኢኮኖሚ ዳግም ለማነቃቃት የሚሰራቸው በርካታ ሥራዎች በግሉ ዘርፍ መደገፍ እንዳለበት ነው ያመላከቱት።
 
እንደ እርሳቸው ገለጻ፤ መንግሥት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ትኩረት ማድረግ አለበት፤ ከዛ በመለስ ያሉ ጉዳዮች ላይ ደግሞ የግሉ ባለኃብት ተሳታፊ በማድረግ መስራት አለበት።
 
በተለይም ደግሞ መንግሥትና የግሉ ባለሀብት በጋራ በመሆን የልማት ፕሮጀክቶችን በሽርክና በመንደፍና በማስፈጸምም ሊተባበሩ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
 
ኢኮኖሚው በአጭር ጊዜ እንዲንሰራራ የመንግሥትን በጀት ብቻ ከመጠቀም ባለፈ በውጭ የሚኖሩ ዳያስፖራዎች ጋርም በትብብር መሥራት ያስፈልጋል ብለዋል።
 
አቅም ያላቸው የዳያስፖራ አባላት ወደ አገራቸው በመምጣት በተለያዩ የልማት መስኮች ላይ ኢንቨሰት እንዲያደርጉ ጥሪ ሊቀርብላቸው እንደሚገባም ነው የተናገሩት፡፡
 
በተለይም በጤና፣ በትምህርት፣ በኢንዱስትሪና በሌሎች የተለያዩ ጉዳዮች ላይ በማሳተፍ የልማት እንቅስቃሴዎችን ማፋጠን እንደሚቻል ያላቸውን እምነት መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
 
መንግሥት ልማትና ሌሎች እንቅስቃሴዎችን ለመደገፍ የሚያወጣቸውን ወጪዎች፥ ጥናትን መሰረት ያደረጉና ወጪ ቆጣቢ ሊሆኑ እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.