Fana: At a Speed of Life!

በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የስነ አዕምሮ እና የስነ ልቦና ህክምና ምላሽ መስጠት የሚያስችል ዘርፈ ብዙ ምላሽ እቅድ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጦርነት እና በተለያዩ ግጭቶች ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የስነ አዕምሮ እና የስነ ልቦና ህክምና ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል የዘርፈ ብዙ ምላሽ እቅድ ይፋ ተደርጓል፡፡
 
የጤና ሚኒስቴር እና የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር በጋራ ያዘጋጁት እቅድ÷ ለባለድርሻ አካላት በኢትዮጵያ የህረተሰብ ጤና ኢንስትቲዩት የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች የመልሶ ማቋቋምና ሪዚሊየንስ ዳይሬክተር ዶ/ር ያረጋል ፉፋ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
 
በቅንጅታዊ ርብርቡ የስነ አዕምሮ፣ የስነ ልቦና እና የማህበራዊ ስራዎች እንዲሁም ለተለያዩ ባለድርሻ አካላት ግንዛቤ የመፍጠር ተግባራት እንደሚከናወኑ ተመላክቷል፡፡
 
 
እቅዱ በማህበረሰብ ደረጃ ድጋፍ የሚሰጡ ልዩ ልዩ ሙያ ያላቸውን ቡድኖች አሰልጥኖ ማሰማረትን፣ በጤና ተቋማት የሚሰጡትን የስነ እዕምሮ ጤና አገልግሎት ማጠናከርን እና በጾታዊ ጥቃት ጉዳት የደረሰባቸውን ሴቶች በጤና ተቋማትና ከጤና ተቋማት ውጪ የጤና እና ስነ ልቦና ድጋፍ አገልግሎት የሚያገኙበትን ስርዓት ማጠናከር እንደሚያስችል ተገልጿል፡፡
 
ለዚህ ስራም እቅዱ ውጤታማነት ሰፊ የባለሙያዎች ቁጥር አሰልጥኖ ማሰማራትን ያካተተ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡
 
በመድረኩ ላይ ከመንግስት አመራሮች፣ ከሙያ ማህበራት፣ ከሀይማኖት ጉባኤ፣ ከዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ ባለሙያዎች እና ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች የተገኙ ሲሆን ተሳታፊዎቹ የቀረበውን እቅድ ሊያዳብሩ የሚችሉ አስተያየቶችን ሰጥተዋል፡፡
የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ÷ በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የጤና ሚኒስቴር የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርግ መቆየቱን አንስተዋል፡፡
 
የሚታዩና የማይታዩ በርካታ ጉዳቶች ሊኖሩ ስለሚችሉ የሚጠበቀው የድጋፍ ስራም በጣም ሰፊ መሆኑን አስረድተው፥ ችግሮችን እንደ አንገብጋቢነታቸው ቅደም ተከተል በማስያዝ ባለው አቅም ቶሎ ወደ ተግባር መግባት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
 
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ በበኩላቸው፥ የአዕምሮና ስነ-ልቦና ችግሮች፣ የመሰረተ ልማቶች ውድመት እና የእሴቶች መሸርሸር ጠለቅ ያሉ ስራዎችን እንደሚጠይቁ ገልጸዋል፡፡
 
የሚፈለገው ውጤት እንዲመጣ እቅዱን ለመተግበር የሚመደበው የሰው ኃይል እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት በሞራል ልዕልና መስራት በጣም ወሳኝ እንደሆነ ማሳሰባቸውን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.