Fana: At a Speed of Life!

በጭላሎ ጋለማ ደን ላይ የእሳት አደጋ በድጋሜ ሲከሰት ፣ በሰሜን ሸዋ ዞን ወፍ ዋሻ ደን ላይ የተከሰተው የእሳት አደጋ እንደቀጠለ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአርሲ ብሔራዊ ተራሮች ፓርክ በጭላሎ ጋለማ ደን ላይ የእሳት አደጋ በድጋሜ ሲከሰት ፣ በሰሜን ሸዋ ዞን ወፍ ዋሻ ደን ላይ የተከሰተው የእሳት አደጋ እንደቀጠለ ነው።
በጭላሎ ተራራ ላይ የተከሰተዉን እሳት ለመቆጣጥር ከፍተኛ ጥረት ቢደረግም እሳቱ ከአቅም በላይ መሆኑን የአረሲ ተራሮች ብሔራዊ ፓረክ አስታውቋል፡፡
ዛሬ ከጠዋት ጀምሮ በአካባቢዉ የተገኙት የህብረተሰብ ክፍሎች የተከሰተዉን እሳት ለማጥፋት ያደረጉት ጥረት ከአቅማችዉ በላይ በመሆኑን ተናረዋል፡፡
ፓርኩ ከሚያካልላቸው ዘጠን ወረዳዎች ውስጥ በዘጠኙ ወረዳዎች ዉስጥ የእሳት አደጋዉ የተከሰተ መሆኑን የአርሲ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ሃላፊ አቶ ሙሀመድ ቲፎ ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡
እሳቱ በፍጥነት እየተጓዘና አብዛኛዎቹን የተራራዉን ክፍል እያካለለ እንደሚገኝ ጣቢያችን በቦታዉ ተገኝቶ ታዝቧል።
ሀላፊዉ እሳቱ ከህብረተሰቡ አቅም በላይ በመሆኑ ለክልሉ ማሳወቃችዉንና አፋጣኝ መፍትሄ እንደሚፈልግ ተናግዋል፡፡
በጭላሎ ተራራ ዉስጥ የሚገኙ ብርቅዬ የዱር አራዊቶች እየተሰደዱና ጉዳት እየደረሰባቸዉ ከመሆኑም በላፈ ረጅም ዘመን ያስቆጠሩ ደኖችም ጉዳት እየደረሰባቸዉ መሆኑን ገልጸዋል ።
በተመሣሣይም በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የሚገኘው ወፍ ዋሻ ደን ላይ የእሳት ቃጠሎ መነሳቱን የአማራ ክልል የአካባቢ ደንና የዱር እንስሳ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር በላይነህ አየለ ገልጸዋል።
የእሳት ቃጠሎው የተነሳው በአንኮበር ወረዳ የደኑ ክፍል ላይ ሲሆን እስካሁን 3 ቀበሌዎችን ያካለለ ሲሆን÷ከአንድ ሺህ ሄክታር በላይ ጉዳት ማድረሱን ነው የተናገሩት።
ቃጠሎውን በአካባቢው ህብረተሰብ እና በክልሉ አቅም ለመቆጣጠር እየተሞከረ ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ በአውሮፕላን ካልታገዘ የማይቻል ነውም ሲሉ ገልጸዋል።
ለዚህም ከፌደራል መንግስት ጋር በመነጋገር ላይ መሆናቸውን አስረድተዋል።
በኦሊያድ በዳኔ እና በዘላለም ገበየሁ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-

https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.