Fana: At a Speed of Life!

በፀጥታ ችግሮች ምክንያት ከ69 ሺህ በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ ሆነዋል-የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ትምህርት ቢሮ

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 28፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በተያዘው የትምህርት ዘመን በፀጥታ ችግሮች ምክንያት ከ69 ሺህ በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸውን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።
ቢሮው የ6 ወራት የዘርፉን አፈፃፀም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መክሯል
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታሁን አብዲሳ በምክክር መድረኩ ላይ ፥ የፀጥታ ችግሩ በክልሉ የትምህርት ዘርፍ ያስከተለውን ተፅዕኖ በመቋቋም ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ስራቸውን እንዲጀምሩ እየተደረገ ነው ብለዋል
በክልሉ የጥፋት ኃይሎች በትምህርት ተቋማት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል ያሉት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ፥ ትምህርት ቤቶች ተጠግነው የመማር ማስተማር ስራው እንዲጀመር ህብረተሰቡና ሁሉም የዘርፉ ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርበዋል።
የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ቢንያም መንገሻ በበኩላቸው፥ በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች የተስተዋሉ የፀጥታ ችግሮች ለትምህርት ዘርፉ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሳቸውን አስታውቀዋል
በፀጥታ ችግሩ 114 የመጀመሪያና አምስት የ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ሙሉ በሙሉ የወደመ ሲሆን፥ 94 የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ደግሞ በከፊል መውደሙን የቢሮ ኃላፊው አስታውቀዋል
የፀጥታ ችግሩ በተያዘው የትምህርት ዘመን በትምህርት ገበታቸው መገኘት የነበረባቸውን ከ69 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ከትምህርት ገበታ ውጭ አርጓቸዋልም ነው ያሉት
አዲሱን ስርዓተ-ትምህርት በክልሉ ገቢራዊ እንዲሆን የሚያስችሉ ቀዳሚ ተግበራት በመከናወን ላይ መሆናቸውንም ገልፀዋል
በክልሉ በትምህርት ዘርፉ በፀጥታ ችግር ምክንያት የደረሱ ጉዳቶቸን በቅንጅት መፍታት የግድ እንደሚልም የምክክር መድረኩ ተሳታፊዎች መግለጻቸዉን ከክልሉ ብዙሃን መገናኛ ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.