Fana: At a Speed of Life!

በፈረንሳይ በኮሮና ቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በፈረንሳይ በኮሮና ቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ይገኛል ተባለ፡፡
 
በሀገሪቱ በትናንትናው ዕለት ብቻ 30 ሺህ 621 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ነው የተነገረው፡፡
 
ይህም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተመዘገበው ትልቁ ቁጥር ነው ተብሏል፡፡
 
ፈረንሳይ እያገረሸ የመጣውን የወረርሽኝ ስርጭት ለመግታት ፓሪስን ጨምሮ በስምንት ከተሞች ነገ የሚጀምር የሰዓት እላፊ ገደብ እንደምትጥል ገልጻለች፡፡
 
ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ሰዓት እላፊ እወጃው በየዕለቱ የሚያዘውን ሰው ቁጥር ወደ 3 ሺህ ዝቅ ያደርጋል ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
 
ከፈረንሳይ በተጨማሪ በጀርመን፣ በጣልያን እና በፖላንድ በየዕለቱ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ እንደሚገኝ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
 
ይህን አስመልክቶ የዓለም ጤና ድርጅት የሰዎችን ህይወት ለመታደግ ጠንካራ የሆነ ክልከላ ማሳለፍ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥቷል፡፡
 
በተለያዩ የአውሮፓ ሃገራት ትምህርት ቤቶች፣ የሰውነት እንቅስቃሴ ማዕከላት፣ ምግብ እና መጠጥ ቤቶች ዳግም እየተዘጉ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.