Fana: At a Speed of Life!

በፈረንሳይ ፓሪስ የ’በቃ’ ንቅናቄ አካል የሆነው የተቃውሞ ሰልፍ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በፈረንሳይ ፓሪስ ‘ሻትሌ ሊሀል’ በተሰኘው ስፍራ የ’በቃ’ #No More ንቅናቄ አካል የሆነው የተቃውሞ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።
 
በሰልፉ ላይ በኢትዮጵያ ላይ እየተደረገ ያለውን ያልተገባ ጫና እንዲሁም አንዳንድ የምዕራባውያን መገናኛ ብዙሃን የሚያሰራጩት የሐሰት፣ የተዛባና ሚዛናዊነት የጎደለውን ዘገባ እንዲያቆሙ የሚጠይቁ መፈክሮች እየተሰሙ ይገኛል።
 
የኢትዮጵያ ኮሙዩኒቲ በፈረንሳይ ምክትል ፕሬዚዳንት ፍሬህይወት ገበየሁ ለኢዜአ እንደገለጹት÷በሰልፉ ላይ የተለያዩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ የሌሎች አፍሪካ ሀገራት ዜጎች ታድመዋል።
 
የሰልፉ አስተባባሪዎች በፈረንሳይ የኢትዮጵያ ኮሙዩኒቲ፣ የኢትዮጵያ ዲፌንስ ታክስ ፎርስ እና የኤርትራ ኮሙዩኒቲ መሆናቸውን ገልጸዋል።
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.