Fana: At a Speed of Life!

በፈረንጆቹ 2021 የመጀመሪያ አጋማሽ የስደተኞች ሞት በእጥፍ ጨምሯል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በፈረንጆቹ 2021 የመጀመሪያ አጋማሽ አመት ለህልፈት የተዳረጉ ስደተኞች ቁጥር በእጥፍ መጨመሩን ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት አስታወቀ፡፡
በፈረንጆቹ በተያዘው ዓመት የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት ውስጥም ቢያንስ 1 ሺህ 146 ሰዎች በባህር ወደ አውሮፓ ለመግባት ሲሞክሩ ለህልፈት መዳረጋቸው ታውቋል፡፡
በ2021 የመጀመሪያ አጋማሽ ላይ የሜዲትራንያንን ባህር በመሻገር መዳረሻቸውን አውሮፓ ለማድረግ ያለሙ 1 ሺህ 146 ስደተኞች ለህልፈት መዳረጋቸውን ድርጅቱ አስታውቋል፡፡
በሊቢያና ጣሊያን መካከል ያለው መካከለኛው የሜዲትራንያን መስመር፣ በምዕራብ አፍሪካና በስፔን የካናሪ ደሴቶች መካከል የአትላንቲክ ውቅያኖስ፣ በምዕራባዊ ሜዲትራንያን ወደ ስፔን የሚወስደው መስመር እንዲሁም በምሥራቅ ሜዲትራኒያን ወደ ግሪክ የሚወስደው መስመር ስደተኞቹ በብዛት ለህልፈት የተዳረጉባቸው መስመሮች ሆነዋል የተባለው፡፡
በአብዛኛዎቹ የነብስ አድን ጀልባዎች ላይ በወደብ አካባቢ የሚፈጸመው አስተዳደራዊ በደል፣ ጥቃት፣ የሰራተኞች እስርና እንግልትም ለስደተኞች ህልፈት መጨመር ምክንያት መሆኑንም ድርጅቱ ገልጿል፡፡
ምንጭ፡-አልጀዚራ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.