Fana: At a Speed of Life!

በፊሊፒንስ መዲና አቅራቢያ እሳተ ገሞራ መፍሰስ መጀመሩን ተከትሎ ማስጠንቀቂያ ተሰጠ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 4 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በፊሊፒንስ መዲና አቅራቢያ እሳተ ገሞራ መፍሰስ መጀመሩን ተከትሎ ነዋሪዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ማስጠንቀቂያ ተሰጠ።

በመጠኑ አነስተኛ የተባለው እና መፍሰስ የጀመረው እሳተ ገሞራ አካባቢውን በአመድ ብናኝ ሸፍኖታል ተብሏል።

የአመድ ብናኙም አየር ላይ እስከ 14 ኪሎ ሜትር ድረስ ይወጣል ነው የተባለው።

ከዚህ ጋር ተያይዞም ወደ ከ450 ሺህ በላይ ነዋሪዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል።

የሃገሪቱ ባለስልጣናት በአካባቢው ከፍተኛ ፍንዳታ ሊከሰትና ከባድ ጉዳት ይደርሳል በሚል ነዋሪዎችን እያስወጡ ነው።

ይህን ተከትሎም አሁን ላይ እሳተ ገሞራው መፍሰስ ከጀመረበት ስፍራ በ17 ኪሎ ሜትር ዙሪያ የሚገኙ ሰዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ታዘዋል።

ባለስልጣናቱ በመጭዎቹ ሰዓታት ወይም ቀናት አደገኛ እሳተ ገሞራ አካባቢው ላይ ሊከሰት እንደሚችልም ፍንጭ ሰጥተዋል።

ፍንዳታው ከተከሰት የእሳተ ገሞራው ብናኝ እና ፍንጣሪዎች እንዲሁም ያንን ተከትሎ የሚፈጠር በካይ ጋዝ ከፍ ያለ ጉዳት እንዳያደርስም ተሰግቷል።

ታዓል እሳተ ገሞራ ከመዲናዋ ማኒላ 60 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከምትገኘው የሉዞን ደሴት የሚነሳ አደገኛ እና ንቁ የሚባል የእሳተ ገሞራ አይነት መሆኑ ይነገራል።

ምንጭ፦ ሲ ኤን ኤን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.