Fana: At a Speed of Life!

በፋና ላምሮት የድምፃዊያን ውድድር ዮናታን ዳመነ አንደኛ በመውጣት የ200 ሺህ ብር አሸናፊ ሆነ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፋና ላምሮት የምዕራፍ 6 የፍፃሜ ውድድር ዛሬ ተካሂዶ ለአሸናፊዎቹ 500 ሺህ ብር ተበርክቷል፡፡

ከ2 ሺህ በላይ የሚሆኑ ወጣት ድምፃውያን የማጣሪያ ውድድር አድርገው፤ ማጣሪያውን ያለፉ 12 ድምፃውያን በየሳምንቱ በቀጥታ የቴሌቪዥን ሥርጭት ከሙሉ የሙዚቃ ባንድ ጋር በመሆን በዳኞችና በእራሳቸው የተመረጡ ዘፈኖችን እያቀረቡ ተወዳድረዋል፡፡

በተመልካች የኤስ ኤም ኤስ ድምጽ እና በሙዚቃ ባለሙያ ዳኞች ነጥብ ዝቅተኛ ያገኝ አንድ ተወዳዳሪ በየሳምንቱ እየተሰናበተ 4 ድምፃውያን ለፍጻሜ ደርሰዋል፡፡

ዛሬ በተካሄደው የፍፃሜ ውድድር እያንዳዱ ድምፃዊ 3 ዘፈኖችን አቅርበው ውድድራቸውን አካሂደዋል፡፡

በዳኞችና በተመልካች ዳኝነቱ ተሰጥቷል፡፡

በዚህም መሰረት ፡-

ድምፃዊ ዮናታን ዳመነ አንደኛ በመውጣት የምዕራፉ አሸናፊ በመሆን የ200 ሺህ ብር አሸናፊ ሆኗል፡፡

ድምፃዊ ሙሉጌታ ለማ ሁለተኛ በመውጣት 150 ሺህ ብር አግኝቷል፡፡

ድምፃዊ ተመስገን በቀለ ሦስተኛ በመውጣት 100 ሺህ ብር እና ድምፃዊ ዘላለም እሸቱ አራተኛ በመውጣት 50 ሺህ ብር አግኝተዋል፡፡

የሮሃ ባንዱ አንጋፋ ሙዚቀኛ  ጆቫኒ  ሪኮ በክብር እንግድነት ተገኝቶ ለአሸናፊዎቹ  ሽልማቱን አበርክቷል፡፡

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አድማሱ ዳምጠው የፍፃሜ ውድድሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት በየምዕራፉ ስህተቶችን እያረመ ጥበብ ከፍ እንድትል ፣ ክብር እንድታገኝ እና ትውልድን ለመቅረፅ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ይህ የድምፃውያን ውድድር ስኬታማ እንዲሆን የበኩላቸውን ሚና ለተወጡ የሙዚቃ ባለሙያዎች ፣ ዳኞች ፣ ለኮርፖሬቱ ሰራተኞች እና አጋር ድርጅቶች ምስጋና አቅርበዋል።

የህብረተሰብ ፕሮግራሞችን በመቅረፅ ህዝብ የሚፈልገውን ዝግጅቶች በማድረስ ላይ እንደሚገኝ እና በቀጣይም ይህንኑ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልፀዋል።

አራቱ ድምፃውያን ከወራት በኋላ ለሚካሄደውና 1 ሚሊየን ብር እና የክብር ዋንጫ ለሚያስገኝው የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር በቀጥታ አልፈዋል፡፡

ከሁለት ሳምንት እረፍት በኋላ የምዕራፍ 7 ውድድር የሚጀምር ሲሆን በውድድሩ ለመሳተፍ ተሰጥዖ እና ልምድ ያላቸው ድምፃውያን ከሚያዝያ 14 እስከ 16 ቀን 2013 ዓ.ም በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዋናው መስሪያ ቤት በአካል በመምጣት አልያም በተጠቀሱት ቀናት 8333 ላይ በመደወል መመዝገብ እንደሚችሉ ጥሪ ተላልፏል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.