Fana: At a Speed of Life!

በፌደራልና በክልል የተጀመረ የለውጥ አካሄድ በቀበሌና ወረዳ መዋቅሮች ሊተገበር ይገባል – ምሁራን

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በፌደራልና በክልል ደረጃ የተጀመረ የለውጥ አካሄድ ህዝብን ፊት ለፊት በሚያገኙት የቀበሌና ወረዳ መዋቅሮች ሊተገበር እንደሚገባ ምሁራን ተናገሩ፡፡
በድሬዳዋ ዩኒቨርሰቲ የፖለቲካል ሳይንስ ምሁሩ ሱራፌል ጌታሁን እንደተናገሩት÷ ህዝብን ለምሬት የዳረጉ የታችኛው የመንግስት መዋቅር አሰራሮችን ለማሻሻል የሀሳብ ብዝሃነትን እንዲያስተናግዱ በሚያስችል ሁኔታ ማዋቀር ይገባል፡፡
ይህንን ችግር ለመፍታት እንዲቻል መስፈርቱ ፓርቲ ብቻ ሳይሆን÷ አቅምና ችሎታ ያላቸውን ግለሰቦች ማሳተፍ ያስፈልጋል ብለዋ፡፡
በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህሩ ዶክተር ደጉ አስረስ በበኩላቸው÷ ታችኞቹ የመንግስት መዋቅሮች በህዝብ የዕለት ተለዕት ግልጋሎት ቁልፍ ሚና አላቸው ብለዋል፡፡
በእነዚህ መዋቅሮች የሚስተዋለው ችግር ግለሰቦችን ወደ ስልጣን በማምጣት ሳይሆን÷ መዋቅራዊ የአሰራር ለውጥን በመተግበር፤ ደግሞም ተጠያቂነትን በማስፈን የሚፈታ ነው፡፡
በተለይም ለስልጣን ያለን አመለካከት ከጥቅም ማካበቻነት ወደ አገልጋይነት መቀየር ያስፈልጋልም ነው ያሉት ምሁራኑ፡፡
በአፈወርቅ እያዩ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.