Fana: At a Speed of Life!

በፌደራል ተቋማት ውስጥ በብልሽት ተጠራቅመው የሚገኙ የተለያዩ ንብረቶች ከነገ ጀምሮ ይመዘገባሉ ተብሏል

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 3፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ከ100 በላይ በሚሆኑ የፌደራል ተቋማት ውስጥ ለበርካታ ጊዜያት በብልሽት ተጠራቅመው የሚገኙ መኪናዎች፣ ማሽነሪዎች፣ ላፕቶፕ እና ኮምፒተሮች እንዲሁም የፈርኒቸር እቃዎች እና ሌሎች ንብረቶችን የመመዝብ መርሃ ግብር ከነገ ጀምሮ ለተከታታይ አራት ቀናት እንደሚካሄድ ተገለጸ፡፡

የመንግስት ንብረት አስተዳደርና ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሃጂ ኢብሳ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት ትርፍ መኪኖችና በቀላል ብልሽት የቆሙትን ወደ ሌሎች ተቋማት እንዲተላለፉ እና አገልግሎት እንዲሰጡ ይደረጋል ብለዋል፡፡

ለዚህ ስራ እንዲረዳም ሃገርአቀፍ ኮሚቴ መዋቀሩን እና ከነገ ጀምሮ በሁሉም የፌደራል ተቋማት በመዘዋወር የመቃኘት ስራ ያከናውናሉም ተብሏል፡፡

ያለ አገልግሎት ቆመው የሚገኙ መኪኖችና ማሽነሪዎች በጨረታ አልያም በሃራጅ ተሸጠው ለመንግስት ገቢ እንዲያስገኙ እንደሚደረግም ዋና ዳይሬክተሩ አሳውቀዋል፡፡

በዚህ ደረጃ ሲሰራ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ በተነገረለት የንብረት ምዝገባው ከሚሸጡ ንብረቶች እስከ 1 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ መታቀዱም ተነግሯል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘም የንብረት ምዝገባውን አስመልክቶ በተሰጠው መግለጫ ወቅት ኤጀንሲው ለተለያዩ አገልግሎትች ወደ ሃገር ያስገባቸው በመጋዘን የሚገኙ ኬሚካሎች ድንገተኛ የመፈንዳት ዕድል ቢገጥማቸው የሚያደርሱትን ጉዳት በተመለከተ ከጋዜጠኞች ለቀረበው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

በምላሻቸውም ከመጋዘኑ እስከ 250 ሜትር ጉዳት ያደርሳል ተብሎ የተሰጠውን ምላሽ ሁለት መገናኛ ብዙኀን እስከ 250 ኪሎ ሜትር ድረስ ጉዳት ያደርሳል በማለት ያሰራጩት ዘገባ ሃሰት በመሆኑ ግርታ የተፈጠረባቸው ዜጎች መረጃው ትክክል ባለመሆኑ ሊሰጉ እንደማይገባም አሳስበዋል፡፡

በመለሰ ምትኩ

 

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.