Fana: At a Speed of Life!

በፌደራል የሰራተኛና ማህበራዊ ዋስትና ኤጄንሲ ደቡብ ምዕራብ ሪጅን ሰራተኞች ለመከላከያ ሰራዊት ደም ለገሱ

 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ምዕራብ ሪጅን፥ በበደሌ፣ በቦንጋ፣ በዳውሮ፣ በሚዛን፣ በመቱና በጋምቤላ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ስር የሚገኙ 213 ሰራተኞች ለመከላከያ ሰራዊት ደም ለግሰዋል።

ሰራተኞቹ ከዚህን ቀደም የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለሰራዊቱ ድጋፍ ማድረጋቸው ተመላክቷል።

በህዝቦቿ የተባባረ ክንድ አገራችን ያጋጠማትን ፈተና በድል ትወጣለች ያሉት ሰራተኞቹ የአገር ህልውናን ለማስከበር በዱር በገደሉ እየተዋደቁ ላሉ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ትልቅ ክብር እንዳላቸው ገልጸዋል።
በፌዴራል ሰራተኛና ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ የደቡብ ምዕራብ ሪጅን ስራ አስኪያጅ አቶ በድሉ መኮንን በበኩላቸው፥ የሃገር ህልውና እስከሚረጋገጥ ድረስ የድርጅኑ ሰራተኞች የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል፡፡

በሙክታር ጠሃ

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.