Fana: At a Speed of Life!

በፌደራል የዳኝነት አስተዳደር እና በፌደራል ፍርድ ቤቶች ረቂቅ አዋጆች ዙሪያ ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በፌደራል የዳኝነት አስተዳደር እና በፌደራል ፍርድ ቤቶች ረቂቅ አዋጆች ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያካሄደ ይገኛል፡፡

በውይይቱ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊን ጨምሮ ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል።

በመድረኩ ስድስት ምዕራፎች እና 47 አንቀጾችን በያዘው የፌደራል የዳኝነት አስተዳደር ረቂቅ አዋጅ ዙሪያ የመነሻ ጽሁፍ መቅረቡን ኢዜአ ዘግቧል።

አዋጁ ጸድቆ ወደ ስራ በሚገባበት ጊዜም የህግ የበላይነት እንዲከበር እና ፍርድ ቤቶች የተሻለ አመኔታ እንዲያገኙ ያስችላል ተብሎ ይጠበቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.