Fana: At a Speed of Life!

በፌዴራል አስተዳደር ስነስርዓት አዋጅ ዙሪያ የተቋማት አተገባበር ግምገማ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 18 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በፌዴራል አስተዳደር ስነስርዓት አዋጅ ዙሪያ የተቋማት አተገባበር ግምገማ እየተካሄደ ነው፡፡

የፍትህ ሚኒስቴር በአስተዳደር ስነስርዓት አዋጅ ዙሪያ የገንዘብ ሚኒስቴር፣ የጤና ሚኒስቴር፣ የገቢዎች ሚኒስቴር እና ጉምሩክ ኮሚሽን አፈጻጸም ክትትል ያደረገ መሆኑም ተመላክቷል፡፡

በመርሐ ግብሩ የፍትህ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ፍቃዱ ጸጋ ፥ የፌዴራል አስተዳደር ስነስርዓት አዋጅ ዜጎች መብትና ግዴታቸውን አውቀው ሀገራቸውን እንዲያሳድጉ ትልቅ አስተዋዕኦ አለው ብለዋል፡፡

የፌዴራል አስተዳደር ስነስርዓት አዋጅ ዜጎች የሚመሩበትን ህግ እንዲያውቁና አዳዲስ መመሪያዎች ሲወጡም ተሳትፎ በማሳደግ መብትና ግዴታቸውን እንዲለዩ ሚናው ከፍ ያለ ነው ብለዋል።

በሀገር የአስተዳደር ተቋማት ላይ የዜጎችን መብት በሚገባ ለማረጋገጥ አዋጁ አስፈላጊ መሆኑንም ነው የጠቀሱት።

በዛሬው ውይይት የገንዘብ ሚኒስቴር፣ የጤና ሚኒስቴር፣ የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽን መመሪያን በማውጣትና በውሳኔዎች ላይ ዜጎችን የማሳተፍ እንዲሁም ህጉን ምን ያህል ተግባራዊ እንዳደረጉ የሚታይበትና በተቋማቱ ላይ የተደረገው የክትትል ሪፖርት እንደሚቀርብ ይጠበቃል።

ውይይቱ የተቋማቱ የአዋጁን አፈጻጸም በማየት፣ ክፍተታቸውን በመገምገም በቀጣይ የዜጎችን ተሳፎቶ ማሳደግ እንዲቻል የቤት ስራ ይዘው የሚሄዱበት እንደሚሆንም ነው የተገለፀው።

በሃይማኖት ኢያሱ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.