Fana: At a Speed of Life!

በፒያሳ አካባቢ በ7 የንግድ ሱቆች ላይ የእሳት አደጋ ደረሰ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ፒያሳ አካባቢ በሚገኙ ሰባት የንግድ ሱቆች ላይ የእሳት አደጋ ደረሰ፡፡

4 ሰዓት ከ40 ደቂቃ ላይ በተከሰተው በዚህ እሳት አደጋ ሰባት ሱቆች ላይ ቃጠሎ የደረሰ ሲሆን፥ ከእነዚህ ውስጥ ሁለት ሱቆች ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ተገልጿል።

የአዲስ አበባ የእሳት አደጋና ስራ አመራር ኮሚሽን በስፍራው በመገኘት እሳቱ ተጨማሪ አደጋ ሳይስከትል መቆጣጠር መቻሉ ተጠቁሟል፡፡

በዚህ አደጋ በሰው ላይ ምንም አይነት ጉዳት ያልደረሰ ሲሆን፥ የአደጋው መንስኤም እየተጣራ ይገኛል።

አደጋው በተከሰተበት ስፍራ ላይ ምግብ ቤቶች፣ የአልባሳት፣ የመነጽር እና የመዋቢያ ቅባት መሸጫ ሱቆች ይገኛሉ።

በፍሬህይወት ሰፊው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.