Fana: At a Speed of Life!

በፓኪስታን 99 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ የመንገደኞች አውሮፕላን ተከሰከሰ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 14 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በፓኪስታን 99 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ የመንገደኞች አውሮፕላን ተከሰከሰ።

አውሮፕላኑ ከላሆር በመነሳት መድረሻውን ጂናህ አድርጎ በመብረር ላይ እያለ ካራቺ ከተማ አቅራቢያ መከስከሱን የሃገሪቱ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በአካባቢው የደረሱ ሲሆን፥ የአደጋው ዝርዝር ሁኔታም እየተጣራ ነው ተብሏል።

የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ደግሞ አብራሪው አውሮፕላኑ የቴክኒክ ችግር እንደገጠመው ሲገልጽ ነበር ብለዋል።

አውሮፕላኑ 91 መንገደኞችን እና 8 የአውሮፕላኑን ሰራተኞችን በውስጡ ይዞ ነበር።

ከአካባቢው የሚወጡ መረጃዎች በአደጋው በርካቶች ሳይሞቱ እንዳልቀረ ያመላክታሉ።

ስሪቱ የኤር ባስ የሆነው ኤ320 አውሮፕላን በጂናህ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ ነበር የተከሰከሰው።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.