Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየር ሊጉ ሊቨርፑል ሲሸነፍ በላ ሊጋ ሪያል ማድሪድ መሪነቱን አጠናክሯል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 26፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በስፔን ላ ሊጋ ትናንት በተደረገ ጨዋታ ሪያል ማድሪድ መሪነቱን ያጠናከረበትን ውጤት አስመዝግቧል።

ማድሪድ ከጌታፌ ተጫውቶ 1 ለ 0 በማሸነፍ ከተከታዩ ባርሴሎና ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት 4 አድርሶታል።

ባርሴሎና ከአትሌቲኮ ማድሪድ ጋር ተጫውቶ ሁለት አቻ መለያየቱ ይታወሳል።

ውጤቱን ተከትሎም ሪያል ማድሪድ በ74 ነጥብ ሲመራ ባርሴሎና በ70 ነጥብ ይከተላል።

በሌላ በኩል አሸናፊው በተለየበት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንቼስተር ሲቲ ሊቨርፑልን 4 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፎታል።

የድል ጎሎቹን ኬቪን ደብሩይነ፣ ራሄም ስተርሊን፣ ፊል ፎደን እና አሌክስ ኦክስላዴ ቻምበርሊን በራሱ መረብ ላይ አስቆጥረዋል።

በሌላ ጨዋታ ቶተንሃም ሆትስፐርስ በሼፊልድ ዩናይትድ ተሸንፏል።

ጨዋታው በሼፊልድ ዩናይትድ 3 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቋል።

በጣሊያን ሴሪ አ ትናንት በተደረገ ጨዋታ አታላንታ ናፖሊን 2 ለ 0 አሸንፏል፣ ኢንተር ሚላን እና ጂቬንቱስ ከትናንት በስቲያ ማሸነፋቸው የሚታወስ ነው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.