Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየር ሊጉ መቐለ 70 እንደርታ መሪነቱን ያጠናከረበትን ውጤት አስመዝግቧል

አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 11ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በክልል ከተሞች እና በአዲስ አበባ ተካሂደዋል።

የፕሪሚየር ሊጉ መሪ መቐለ 70 እንደርታ መቐለ ላይ ከስሑል ሽረ ያደረገውን ጨዋታ 1 ለ 0 በማሸነፍ መሪነቱን አጠናክሯል።

ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ፋሲል ከነማ ወደ ጅማ አቅንቶ ከጅማ አባ ጅፋር ጋር 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይቷል፡፡

ሁለቱም አዲስ የፕሪሚየር ሊግ ቡድኖች ያገናኘው የሀድያ ሆሳዕና እና የወልቂጤ ከተማ ጨዋታ በእንግዳው ወልቂጤ ከተማ 2 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቋል።

ድሬዳዋ ከተማ ሰበታ ከተማን አስተናግዶ 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡

ሀዋሳ ከተማ ወላይታ ዲቻን እንዲሁም ባህርዳር ከተማም አዳማ ከተማን 2 ለ 1 ማሸነፍ ችለዋል።

ኢትዮጵያ ቡና እና ከቅዱስ ጊዮርጊስ ያደረጉት የሸገር ደርቢ በአዲስ አበባ ስታድየም የተካሄደ ሲሆን በዚህም ቅዱስ ጊዮርጊስ 1 ለ 0 አሸንፏል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.