Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየር ሊጉ ሰበታ ከተማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ሳምንት ጨዋታ ዛሬ ተካሄዷል፡፡

ረፋድ ላይ ሃዋሳ ከተማ ከተማን ከሰበታ ከተማ ባገናኘው ጨዋታ ሰበታ ከተማ ድል ቀንቶታል፡፡

ጨዋታውን ሰበታ 3 ለ 1 ሲያሸንፍ አለማየሁ ሙለታ፣ ዳዊት እስጢፋኖስ እና ፉአድ ፈረጃ የድል ጎሎቹን አስቆጥረዋል፡፡

መስፍን ታፈሰ ደግሞ ለሃዋሳ ከተማ የማስተዛዘኛዋን ጎል አስቆጥሯል፡፡

ከሰአት በኋላ በተደረገ ጨዋታ ደግሞ ቅዱስ ጊዮርጊስ ድሬዳዋ ከተማን በተመሳሳይ 3 ለ 1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል፡፡

አቤል ያለው፣ አዲስ ግደይ እና ከነዓን ማርክነህ ለፈረሰኞቹ የድል ጎሎቹን አስቆጥረዋል፡፡

የድሬዳዋ ከተማ ብቸኛ ጎል ደግሞ በሙህዲን ሙሳ ተመዝግባለች፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.