Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየር ሊጉ ቶተንሃም በላ ሊጋው ደግሞ ባርሴሎና ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ ፣ሰኔ 17፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ትናንት ምሽት በአውሮፓ ታላላቅ ሊጎች የሃገር ውስጥ ውድድሮች ተካሄደዋል።

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሁለት ጨዋታዎች ተደርገው ቶተንሃም ሆትስፐርስ ድል ቀንቶታል።

ቀደም ብሎ በተደረገ ጨዋታ በሜዳው ብራይተንን ያስተናገደው ሌሲስተር ሲቲ ጨዋታውን ያለምንም ጎል በአቻ ውጤት ጨርሷል።

በጨዋታው ብራይተኖች ያገኙት የፍጹም ቅጣት ምት በሌሲስተሩ ግብ ጠባቂ ካስፐር ሽማይክል ጎል ከመሆን ድኗል።

በሌላ ጨዋታ ቶተንሃም ሆስትሰፐርስ ዌስትሃም ዩናይትድን 2 ለ 0 አሸንፏል።

በጫዋታው እንግሊዛዊው አጥቂ ሃሪ ኬን ከረጅም ጊዜ በኋላ የመጀመሪያ ጎሉን ሲያስቆጥር የዌስትሃሙ ሱሴክ በራሱ መረብ ላይ ሁለተኛዋን ጎል አስቆጥሯል።

ማንቼስተር ዩናይትድ ከሼፊልድ ዩናይትድ፣ ኒውካስትል ከአስተንቪላ፣ ኖርዊች ከኤቨርተን፣ ወልቭስ ከበርንማውዝ እንዲሁም ሊቨርፑል ከክሪስታል ፓላስ ደግሞ የዛሬ መርሃ ግብሮች ናቸው።

በሌላ በኩል በስፔን ላ ሊጋ ባርሴሎና በኢቫን ራኪቲች ጎል አትሌቲክ ቢልባኦን 1 ለ 0 አሸንፏል።

ከሜዳው ውጭ ከሌቫንቴ የተጫወተው አትሌቲኮ ማድሪድም በተመሳሳይ 1 ለ 0 ሲያሸንፍ ሪያል ቫያዶሊድ ከጌታፌ አንድ አቻ ተለያይተዋል።

በጣሊያን ሴሪ አ ደግሞ ናፖሊ ከሜዳው ውጭ ሄላስ ቬሮናን 2 ለ 0፣ ፓርማ ጄኖዋን 4 ለ 1፣ ካግሊያሪ ስፓልን እንዲሁም ቶሪኖ ዩዲኒዜን በተመሳሳይ 1 ለ 0 አሸንፈዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.